15. የተስፋዪቱ ምድር

15. የተስፋዪቱ ምድር — illustration 1

በመጨረሻ እስራኤላውያን ወደ ተስፋዪቱ ምድር፣ ወደ ከነዓን የሚገቡበት ጊዜ ደረሰ። ኢያሱ በብርቱ ግንብ ተጠብቃ ወደ ነበረችው የከነዓናውያን ከተማ ኢያሪኮ ሁለት ሰላዮችን ላከ። በዚያች ከተማ ሰላዮቹን የሸሸገችና ኋላ ላይ እንዲያመልጡ የረዳቻቸው ረዓብ የተባለች ጋለሞታ ትኖር ነበር። እርስዋ በእግዚአብሔር ስላመነች ይህን አደረገች። ሰላዮቹ፣ እስራኤላውያን ኢያሪኮን በሚያጠፉበት ጊዜ ረዓብንና ቤተ ሰብዋን እንደሚያድኑአቸው ቃል ገቡላት።

15. የተስፋዪቱ ምድር — illustration 2

እስራኤላውያን ወደ ተስፋዪቱ ምድር ለመግባት የዮርዳኖስን ወንዝ መሻገር ነበረባቸው። እግዚአብሔር፣ “መጀመሪያ ካህናቱ እንዲሻገሩ አድርግ” ብሎ ለኢያሱ ነገረው። ካህናቱ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መግባት በጀመሩ ጊዜ፣ እስራኤላውያን በደረቅ መሬት መሻገር ይችሉ ዘንድ ከላይ በኩል የነበረው ውሃ መፍሰሱን አቆመ።

15. የተስፋዪቱ ምድር — illustration 3

ሕዝቡ የዮርዳኖስን ወንዝ ከተሻገሩ በኋላ፣ እግዚአብሔር ኃይለኛውን የኢያሪኮ ከተማ እንዴት እንደሚወጋት ለኢያሱ ነገረው። ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ታዘዙ። ወታደሮቹና ካህናቱ ልክ እግዚአብሔር እንደ ነገራቸው በቀን አንዴ ለስድስት ቀናት የኢያሪኮን ከተማ ዞሩ።

15. የተስፋዪቱ ምድር — illustration 4

ከዚያም በሰባተኛው ቀን፣ እስራኤላውያን ሰባት ጊዜ ከተማይቱን ዞሩ። ለመጨረሻ ጊዜ ከተማዪቱን እየዞሩ እያሉ ወታደሮቹ ጮኹ፣ ካህናቱም መለከቶቻቸውን ነፉ።

15. የተስፋዪቱ ምድር — illustration 5

ከዚያም በኢያሪኮ ዙሪያ የነበረው ግንብ ወደቀ! እግዚአብሔር እንዳዘዘው እስራኤላውያን በከተማይቱ የነበረውን ነገር ሁሉ አጠፉ። የእስራኤላውያን ወገን የሆኑትን ረዓብንና ቤተ ሰብዋን ብቻ አዳኑአቸው። በከነዓን የሚኖሩ ሌሎች ሕዝቦች እስራኤላውያን ኢያሪኮን እንዳጠፉአት በሰሙ ጊዜ፣ እስራኤላውያን እነርሱንም ደግሞ እንደሚወጉአቸው በማሰብ ፈሩ።

15. የተስፋዪቱ ምድር — illustration 6

እግዚአብሔር በከነዓን ካሉ ከማናቸውም የሕዝብ ወገኖች ጋር የሰላም ስምምነት እንዳያደርጉ እስራኤላውያንን አዞአቸው ነበር። ነገር ግን ገባዖናውያን የተባሉት ከከነዓናውያን ሕዝብ ወገኖች አንዱ የሆኑት፣ ከከነዓን ራቅ ብሎ ከሚገኝ ቦታ የመጡ መሆናቸውን ለኢያሱ ዋሽተው ነገሩት። ከእነርሱ ጋር የሰላም ስምምነት እንዲያደርግ ኢያሱን ጠየቁት። ገባዖናውያን ከየት እንደ ሆኑ ኢያሱና እስራኤላውያን እግዚአብሔርን አልጠየቁም። ስለዚህ ኢያሱ ከእነርሱ ጋር የሰላም ስምምነት አደረገ።

15. የተስፋዪቱ ምድር — illustration 7

ገባዖናውያን እንዳታለሉአቸው ባወቁ ጊዜ፣ እስራኤላውያን ተናደዱ፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት የገቡት ቃል ስለ ነበር፣ ከእነርሱ ጋር ያደረጉትን የሰላም ስምምነት ጠበቁ። ቆየት ብሎ በሌላ ጊዜ፣ በከነዓን የነበሩ ሌላ ሕዝብ ወገን ነገሥታት፣ አሞራውያን፣ የገባዖን ሰዎች ከእስራኤላውያን ጋር የሰላም ስምምነት እንዳደረጉ ሰሙ፣ ስለዚህ ጦር ሠራዊታቸውን አንድ ላይ አስተባበሩና ገባዖናውያንን ወጉ። ገባዖናውያን እርዳታ ጥየቃ ወደ ኢያሱ መልእክት ላኩ።

15. የተስፋዪቱ ምድር — illustration 8

ስለዚህ ኢያሱ የእስራኤልን ጦር ሠራዊት ሰበሰበና ወደ ገባዖናውያን ለመድረስ ሌሊቱን ሙሉ ተጓዙ። በማለዳ ሳያስቡት የአሞራውያንን ጦር ሠራዊት ወጉ።

15. የተስፋዪቱ ምድር — illustration 9

በዚያን ቀን እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተዋጋ። አሞራውያንን አደናገራቸውና ትልልቅ የበረዶ ድንጋይ ልኮ ከአሞራውያን ብዙዎችን ገደለ።

15. የተስፋዪቱ ምድር — illustration 10

ደግሞ እግዚአብሔር እስራኤል አሞራውያንን ፈጽመው ለማሸነፍ በቂ ጊዜ ይኖራቸው ዘንድ ፀሐይ በሰማይ በአንድ ቦታ እንድትዘገይ አደረገ። በዚያን ቀን እግዚአብሔር ለእስራኤል ታላቅ ድል አጐናጸፋቸው።

15. የተስፋዪቱ ምድር — illustration 11

እግዚአብሔር እነዚያን ጦር ሠራዊት ካሸነፈ በኋላ፣ ብዙዎቹ የከነዓናውያን ሕዝብ ወገኖች እስራኤልን ለመውጋት በአንድነት ተሰበሰቡ። ኢያሱና ሌሎቹ እስራኤላውያን ወጉና አሸነፉአቸው።

15. የተስፋዪቱ ምድር — illustration 12

ከዚህ ጦርነት በኋላ እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ነገድ ከተስፋዪቱ ምድር የሚደርሰውን ክፍል ሰጠው። ከዚያም እግዚአብሔር ለእስራኤል በድንበሮችዋ ሁሉ ሰላምን ሰጣት።

15. የተስፋዪቱ ምድር — illustration 13

ኢያሱ ባረጀ ጊዜ፣ የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ አንድ ላይ ጠራ። ከዚያም ኢያሱ እግዚአብሔር በሲና ከእስራኤላውያን ጋር ላደረገው ቃል ኪዳን እንዲታዘዙ ለሕዝቡ ግዴታቸውን አስታወሳቸው። ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው ለመኖርና ሕግጋቱን ለመከተል ቃል ገቡ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከኢያሱ 1-24።

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).