18. የተከፈለው መንግሥት

18. የተከፈለው መንግሥት — illustration 1

ከብዙ ዓመታት በኋላ፣ዳዊት ሞተ፣ ልጁ ሰሎሞንም በእስራኤል ላይይገዛ ጀመር። እግዚአብሔር ለሰሎሞን ተናገረውና በይበልጥ ምን እንደሚፈልግ ጠየቀው። ሰሎሞን ጥበብን በለመነጊዜ፣ በዓለም ላይእጅግ በጣም ጠቢብ ሰው አደረገው። ሰሎሞን ብዙ ነገሮችን ተማረናበጣም ጠቢብ ፈራጅ ሆነ። ደግሞም እግዚአብሔርበጣም ባለ ጠጋ አደረገው።

18. የተከፈለው መንግሥት — illustration 2

ሰሎሞን በኢየሩሳሌም አባቱ ዳዊት ያቀደውንና ለግንባታው የሚያስፈልጉ ነገሮች የሰበሰበለትን ቤተ መቅደሱን ሠራ። አሁን ሕዝቡ በመገናኛው ድንኳ ፈንታ በቤተ መቅደሱ እግዚአብሔርን አመለኩ መሥዋዕትንም አቀረቡለት። እግዚአብሔር መጥቶ በቤተ መቅደሱ ተገኘ፣ በዚያም ከሕዝቡ ጋር ኖረ።

18. የተከፈለው መንግሥት — illustration 3

ነገር ግን ሰሎሞን ከሌሎች አገሮች የሆኑ ሴቶችን ወደደ። ከሞላ ጐደል 1000 የሚሆኑ ብዙ ሴቶችን በማግባት ለእግዚአብሔር አልታዘዘም! ከእነዚህ ሴቶች ብዙዎቹ ከውጪ አገሮች መጡ፣ ጣዖቶቻቸውን አመጡና እነርሱኑ ማምለካቸውን ቀጠሉ። ሰሎሞን በሸመገለ ጊዜ፣ እርሱም ደግሞ የእነርሱን አማልክት አመለከ።

18. የተከፈለው መንግሥት — illustration 4

እግዚአብሔር በሰሎሞን ላይ ተቈጣ፣ ሰሎሞን ባለመታመኑ እንደ መቀጣጫ ሰሎሞን ከሞተ በኋላ የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ሁለት መንግሥታት እንደሚከፍል ተናገረ።

18. የተከፈለው መንግሥት — illustration 5

ሰሎሞን ከሞተ በኋላ ልጁ ሮብዓም ነገሠ። ሮብዓም ሞኝ ነበረ። የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ንጉሥነቱን ሊያጸድቁለት ተሰብስበው መጡ። ሰሎሞን ብዙ ከባድ ሥራ እንዳሠራቸውና ብዙ ግብር እንዳስከፈላቸው ለሮብዓም ቅሬታቸውን ተናገሩ።

18. የተከፈለው መንግሥት — illustration 6

ሮብዓም በሞኝነት እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ “አባቴ ሰሎሞን ከባድ ሥራ አሠርቶናል ብላችሁ ዐስባችኋል፣ ነገር ግን እኔ ከእርሱ የባሰ ከባድ ሥራ አሠራችኋለሁ፣ ከእርሱ የባሰም በኃይል እቀጣችኋለሁ።”

18. የተከፈለው መንግሥት — illustration 7

ዐሥሩ የእስራኤል ሕዝብ ነገዶች በሮብዓም ላይ ዓመፁ። ሁለት ነገዶች ብቻ ለእርሱ ባላቸው ታማኝነት ቀጠሉ። እነዚህ ሁለት ነገዶች የይሁዳ መንግሥት ሆኑ።

18. የተከፈለው መንግሥት — illustration 8

በሮብዓም ላይ ያመፁት ሌሎቹ ዐሥር የእስራኤል ሕዝብ ነገዶች ኢዮርብዓም የተባለውን ሰው ንጉሣቸው አድርገው ሾሙት። በምድሪቱ ሰሜናዊ ክፍል መንግሥታቸውን አቋቋሙ የእስራኤል መንግሥት ተብለውም ተጠሩ።

18. የተከፈለው መንግሥት — illustration 9

ኢዮርብዓም በእግዚአብሔር ላይ ዓመፀና ሕዝቡ ኃጢአት እንዲሠሩ አደረገ። በይሁዳ መንግሥት ባለው ቤተ መቅደስ እግዚአብሔርን በማምለክ ፈንታ ሕዝቡ ያመልኩአቸው ዘንድ ሁለት ጣዖታትን ሠራላቸው።

18. የተከፈለው መንግሥት — illustration 10

የይሁዳና የእስራኤል መንግሥታት ጠላቶች ሆኑና ብዙ ጊዜ እርስ በርስ ተዋጉ።

18. የተከፈለው መንግሥት — illustration 11

በዐዲሲቱ የእስራኤል መንግሥት፣ ነገሥታቱ ሁሉ ክፉዎች ነበሩ። ከእነዚህ ነገሥታት አብዛኞቹ፣ በእነርሱ ቦታ መንገሥ በፈለጉ ሌሎች እስራኤላውያን ተገደሉ።

18. የተከፈለው መንግሥት — illustration 12

ነገሥታቱ ሁሉና አብዛኞቹ የእስራኤል መንግሥት ሕዝብ ጣዖትን አመለኩ። የጣዖት አምልኮአቸው ብዙውን ጊዜ ግብረ ገብነት የጐደለው የግብረ ሥጋ ግንኙነትና አንዳንድ ጊዜ ልጆችን መሠዋትን ያካተተ ነበር።

18. የተከፈለው መንግሥት — illustration 13

የይሁዳ ነገሥታት የዳዊት ዝርያዎች ነበሩ። ከእነዚህ ነገሥታት አንዳንዶቹ በትክክል የገዙና እግዚአብሔርን ያመለኩ ጥሩ ሰዎች ነበሩ። ነገር ግን አብዛኞቹ ነገሥታት ክፉዎችና ብልሹዎች ነበሩ፣ ጣዖታትንም ያመልኩ ነበር። አንዳንዶቹ ነገሥታት ልጆቻቸውን እንኳ ለሐሰት አማልክት ሠውተዋል። ደግሞም አብዛኞቹ የይሁዳ ሕዝብ በእግዚአብሔር ላይ ዓመፁ ሌሎች አማልክትንም አመለኩ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከ1ኛ ነገሥት 1-6፤ 11-12።

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).