23. የኢየሱስ ልደት

23. የኢየሱስ ልደት — illustration 1

ማርያም ዮሴፍ ለተባለ ጻድቅ ሰው ታጭታ ነበር። እጮኛዋ ዮሴፍ ማርያም መፀነስዋን በሰማ ጊዜ፣ ሕፃኑ የእርሱ እንዳልሆነ ዐወቀ። ማርያምን ለማሳፈር አልፈለገም፣ ስለዚህ ዝም ብሎ ሊፈታት ዐሰበ። ያንን ከማድረጉ በፊት መልአክ መጣና በሕልም ተናገረው።

23. የኢየሱስ ልደት — illustration 2

መልአኩ እንዲህ አለ፡- “ዮሴፍ፣ ማርያምን ሚስት አድርገህ ለመውሰድ አትፍራ። በውስጥዋ ያለው ሕፃን ከመንፈስ ቅዱስ ነው። ወንድ ልጅ ትወልዳለች። ስሙን ኢየሱስ ብለህ ጥራው (ትርጕሙም፣ ‘ያሕዌ ያድናል’ ማለት ነው)፣ ምክንያቱም ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል።”

23. የኢየሱስ ልደት — illustration 3

ስለዚህ ዮሴፍ ማርያምን አገባትና ሚስቱ አድርጎ ወደ ቤቱ ወሰዳት፣ ነገር ግን እስክትወልድ ድረስ ከእርስዋ ጋር አልተኛም።

23. የኢየሱስ ልደት — illustration 4

ማርያም የምትወልድበት ጊዜ እንደ ደረሰ፣ የሮማ መንግሥት ሁሉም ሰው ለቈጠራ ቅድማያቶቹ ወደ ኖሩበት ከተማ እንዲሄድ ተናገረ። ዮሴፍና ማርያም ከሚኖሩበት ከናዝሬት ወደ ቤተ ልሔም ረጅም ጕዞ ተጓዙ ምክንያቱም በቤተ ልሔም ከተማ የተወለደው ቅድማያታቸው ዳዊት ነበረ።

23. የኢየሱስ ልደት — illustration 5

ወደ ቤተ ልሔም በደረሱ ጊዜ ማረፊያ ስፍራ አልነበረም። ሊያገኙ የቻሉት ብቸኛ ክፍል እንስሶች የሚያድሩበት ስፍራ ነበረ። ሕፃኑ በተወለደ ጊዜ የሚያስተኙበት አልጋ ስላልነበረ እናቱ በከብቶች መመገቢያ ገንዳ አስተኛችው። ስሙንም ኢየሱስ አሉት።

23. የኢየሱስ ልደት — illustration 6

በዚያ ሌሊት በአቅራቢያው ባለ ሜዳ ላይ መንጎቻቸውን የሚጠብቁ ጥቂት እረኞች ነበሩ። በድንገት የሚያበራ መልአክ ታያቸው፣ እነርሱም ፈሩ። መልአኩ፣ “አትፍሩ፣ ምክንያቱም ለእናንተ የምሥራች አለኝ። መሲሑ፣ ጌታ በቤተልሔም ተወልዶአል!” አለ።

23. የኢየሱስ ልደት — illustration 7

“ሄዳችሁ ሕፃኑን ፈልጉ፣ በጨርቅ ተጠቅልሎና በእንስሶች መመገቢያ ገንዳ ተኝቶ ታገኙታላችሁ።” ድንገትም ሰማያት በመላእክት ተሞሉ፣ እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ “ክብር ለእግዚአብሔር በሰማይ ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ!” አሉ።

23. የኢየሱስ ልደት — illustration 8

እረኞች ኢየሱስ ወደ ነበረበት ስፍራ ፈጥነው ደረሱና ልክ መልአኩ እንደ ነገራቸው በእንስሶች መመገቢያ ገንዳ ተኝቶ አገኙት። በጣም ደስ አላቸው። ማርያምም ደግሞ በጣም ደስ አላት። እረኞቹ ስለ ሰሙትና ስላዩት ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ፣ በጎቻቸው ወደ ነበሩባቸው ሜዳዎች ተመለሱ።

23. የኢየሱስ ልደት — illustration 9

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከሩቅ ምሥራቅ አገሮች የሆኑ ጠቢባን በሰማይ አንድ ያልተለመደ ኮከብ ዐዩ። ዐዲስ የአይሁድ ንጉሥ የተወለደ መሆኑን እንደሚያመለክት ተገነዘቡ። ስለዚህ ይህንን ንጉሥ ለማየት በጣም ረጅም ርቀት ተጓዙ። ወደ ቤተ ልሔም መጡና ኢየሱስና ወላጆቹ የነበሩበትን ቤት አገኙት።

23. የኢየሱስ ልደት — illustration 10

ጠቢባኑ ኢየሱስን ከእናቱ ጋር ባዩት ጊዜ ወድቀው ሰገዱለት። ለኢየሱስ ውድ ስጦታዎች ሰጡት። ከዚያም ወደ አገራቸው ተመለሱ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 1፤ ሉቃስ 2።

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).