25. ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው

25. ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው — illustration 1

ኢየሱስ ከተጠመቀበኋላ ወዲያውኑ፣ መንፈስቅዱስ ወደምድረ በዳ ወሰደው፣ እዚያምአርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመ። ከዚያም ሰይጣን ወደ ኢየሱስመጣና ኃጢአት እንዲሠራ ኢየሱስን ፈተነው።

25. ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው — illustration 2

“የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንክ፣ መብላት ትችል ዘንድ እነዚህን ድንጋዮች ወደእንጀራ ለውጥ” በማለት ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው።

25. ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው — illustration 3

ኢየሱስ፣ “‘ሰዎች ለመኖር እንጀራ ብቻ አያስፈልጋቸውም፣ነገር ግን እግዚአብሔር የሚናገረው እያንዳንዱ ቃል ያስፈልጋቸዋል’ተብሎ በእግዚአብሔር ቃል ተጽፎአል!” ብሎ መለሰለት።

25. ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው — illustration 4

ከዚያም ሰይጣን ኢየሱስን ወደ ቤተ መቅደስ ጫፍ ወሰደውና፣ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ ራስህን ወደ ታች ወርውር፣ ምክንያቱም፣ ‘ድንጋይ እግርህን እንዳይመታህ ይሸከሙህዘንድ እግዚአብሔር መላእክቱንያዛል ተብሎ ተጽፎል’” አለ።

25. ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው — illustration 5

ነገር ግን ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ቃል በመጥቀስ ለሰይጣን መለሰለት። “በእግዚአብሔር ቃል፣ ‘ጌታ አምላክህን አትፈታተነው’ በማለት ሕዝቡን ያዛል አለ።’”

25. ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው — illustration 6

ከዚያም ሰይጣን የዓለምን መንግሥታትና ክብራቸውን ሁሉ ዐሳየውና፣ “ወድቀህ ብትሰግድልኝይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ” አለ።

25. ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው — illustration 7

ኢየሱስ፣ “ሂድ፣ አንተ ሰይጣን! በእግዚአብሔር ቃልሕዝቡን፣ ‘ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻአምልክ’ ብሎአዞአል” አለው።

25. ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው — illustration 8

ኢየሱስ ለሰይጣንፈተና አልተሸነፈም፣ ስለዚህ ሰይጣን ተወው። ከዚያ በኋላ መላእክት መጥተው ኢየሱስን አገለገሉት።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 4፡1-11፤ ማርቆስ 1፡12-13፤ ሉቃስ 4፡1-13።

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).