10. ዐሥሩ መቅሠፍቶች

10. ዐሥሩ መቅሠፍቶች — illustration 1

ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄዱ። “የእስራኤል አምላክ ‘ሕዝቤንልቀቅ !’” ይላሃል አሉት። ፈርዖን አልሰማቸውም። እስራኤላውያን ነጻ ሆነው እንዲሄዱ በማድረግፈንታ ከዚህም የከበደ ሥራ እንዲሠሩ አስገደዳቸው!

10. ዐሥሩ መቅሠፍቶች — illustration 2

ፈርዖን ሕዝቡን አልለቅም ማለቱን ቀጠለ፣ ስለዚህ እግዚአብሔር በግብፅ ላይ ዐሥር መቅሠፍቶችን ላከ። እግዚአብሔር በእነዚህ መቅሠፍቶች በኩል ከፈርዖንና ከግብፅ አማልክት ሁሉ ይልቅ ኃያል መሆኑን ለፈርዖን ዐሳየው።

10. ዐሥሩ መቅሠፍቶች — illustration 3

እግዚአብሔር የዓባይን ውሃ ወደ ደም ለወጠው፣ ነገር ግን ፈርዖን አሁንም እስራኤላውያንን አልለቀቃቸውም።

10. ዐሥሩ መቅሠፍቶች — illustration 4

እግዚአብሔር በግብፅ ሁሉ ላይ እንቁራሪቶችን ላከ። ፈርዖን ሙሴን እንቁራሪቶቹን እንዲያርቅ ለመነው። ሆነም ቀረ ግን እንቁራሪቶቹ ሁሉ ሞቱ። ፈርዖን ልቡን አደነደነና እስራኤላውያንን ከግብፅ እንዲወጡ አልለቀቃቸውም።

10. ዐሥሩ መቅሠፍቶች — illustration 5

ስለዚህ እግዚአብሔር ትንኞችን ላከ። ከዚያም ዝንቦችን ላከ። ፈርዖን ሙሴንና አሮንን ጠራና መቅሠፍቱን ካቆሙ እስራኤላውያን ከግብፅ መሄድ እንደሚችሉ ነገራቸው። ሙሴ በጸለየ ጊዜ እግዚአብሔር ዝንቦችን ሁሉ ከግብፅ አስወገደ። ነገር ግን ፈርዖን ልቡን አደነደነና ሕዝቡን አልለቀቀም።

10. ዐሥሩ መቅሠፍቶች — illustration 6

ቀጥሎ እግዚአብሔር የግብፃውያን ከብቶች ሁሉ ታመው እንዲሞቱ አደረገ። ነገር ግን የፈርዖን ልብ ደነደነና እስራኤላውያንን አልለቀቀም።

10. ዐሥሩ መቅሠፍቶች — illustration 7

ከዚያም እግዚአብሔር በፈርዖን ፊት ዐመድ ወደ ሰማይ እንዲበትን ለሙሴ ነገረው። ዐመዱን በበተነ ጊዜ በግብፃውያን ላይ የሚያም ቊስል ሆነ፣ በእስራኤላውያን ላይ ግን ቊስሉ አልሆነባቸውም። እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አደነደነ፣ ፈርዖንም እስራኤላውያንን አልለቀቀም።

10. ዐሥሩ መቅሠፍቶች — illustration 8

ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር በግብፅ ያለውን አብዛኛውን ቡቃያ ያጠፋና ከቤት ውጪ የነበረውን ማንኛውንም ሰው የገደለ በረዶ ላከ። ፈርዖን ሙሴንና አሮንን ጠርቶ፣ “በድዬአለሁ። መሄድ ትችላላችሁ” ብሎ ነገራቸው። ስለዚህ ሙሴ ጸለየ፣ በረዶውም ከሰማይ መዝነቡን አቆመ።

10. ዐሥሩ መቅሠፍቶች — illustration 9

ነገር ግን ፈርዖን እንደ ገና ኃጢአት ሠራ ልቡንም አደነደነ። እስራኤላውያንን አልለቀቀም።

10. ዐሥሩ መቅሠፍቶች — illustration 10

ስለዚህ እግዚአብሔር በግብፅ ላይ የአንበጣዎችን መንጋ አመጣ። እነዚህ አንበጣዎች በረዶው ያላጠፋውን ሰብል ሁሉ በሉት።

10. ዐሥሩ መቅሠፍቶች — illustration 11

ከዚያም እግዚአብሔር ለሦስት ቀን የቆየ ጨለማ ላከ። ግብፃውያን ከቤቶቻቸው እስከማይወጡ ድረስ በጣም ጨልሞ ነበር። እስራኤላውያን በሚኖሩበት ስፍራ ግን ብርሃን ነበረ።

10. ዐሥሩ መቅሠፍቶች — illustration 12

ከእነዚህ ዘጠኝ መቅሠፍቶች በኋላ እንኳ ፈርዖን አሁንም እስራኤላውያንን አልለቅም አለ። ፈርዖን ስለማይሰማ፣ እግዚአብሔር አንድ የመጨረሻ መቅሠፍት ለመላከ ወሰነ። ይህ የፈርዖንን ዐሳብ ይለውጣል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘጸአት 5-10።

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).