9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው

9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው — illustration 1

ዮሴፍ ከሞተ በኋላ ዘመዶቹ በሙሉ በግብፅ ቆዩ። እነርሱና ዘሮቻቸው ለብዙ ዓመታት እዚያ መኖራቸውን ቀጠሉ፤ ብዙ ልጆችንም አፈሩ፤ እነርሱ እስራኤላውያን ተብለው ተጠሩ።

9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው — illustration 2

ከመቶዎች ዓመታት በኋላ የእስራኤላውያን ቊጥር እየበዛ መጣ። ግብፃውያንም ዮሴፍንና እነርሱን ለመርዳት ያደረገውን ሁሉ ዘነጉ። እስራኤላውያን እየበዙ በመምጣታቸው ግብፃውያን ፈሯቸው። ስለዚህ በዚያን ጊዜ ግብፅን ያስተዳድር የነበረው ፈርዖን እስራኤሎችን ለግብፃውያን ባሪያዎች አደረጓቸው።

9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው — illustration 3

ግብፃውያን እስራኤላውያንን የግንብ ሥራ እንዲሠሩ፣ ከተማውን ሁሉ እንዲገነቡ በማድረግ በኃይል ያስገድዷቸው ነበር። ከባድ ሥራ ሕይወታቸውን አስቸጋሪ አደረገው። እግዚአብሔር ግን ባረካቸው ብዙ ልጆችም ነበሯቸው።

9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው — illustration 4

ፈርዖን እስራኤላውያን ብዙ ሕፃናት እንዳሏቸው አየ፤ ስለዚህ ፈርዖን ከእስራኤላውያን ወንዶች ልጆች ሲወለዱ አባይ ወንዝ ውስጥ በመወርወር እንዲገድሉ ሕዝቡን አዘዘ።

9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው — illustration 5

አንዲት እስራኤላዊት ሴት ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርሷና ባለቤቷ የቻሉትን ያህል ልጁን ደበቁ።

9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው — illustration 6

የልጁ ወላጆች ልጁን ሊደብቁት ባልቻሉ ጊዜ ልጁን በሚንሳፈፍ ቅርጫት ውስጥ አድርገው በአባይ ወንዝ ዳር ባለው ቄጤማ ፊት ለፊት እንዳይገደል ሊያድኑት ወንዙ ላይ ለቀቁት። ታላቅ እህቱም የሚሆንበትን ለማየት በቅርብ ትከታተለው ነበር።

9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው — illustration 7

የፈርዖን ሴት ልጅ ቅርጫት አየችና በውስጡ ያለውን ተመለከተች። ሕፃኑን ባየች ጊዜ እንደ ልጇ አድርጋ ወሰደችው። እርሷም ልጁን የምትንከባከብ እስራኤላዊት ሴት ቀጠረች። የቀጠረቻትም ሴትዮ የገዛ ልጁ እናት መሆኗን ሳታውቅ ነበር። ልጁም ሲያድግና የናቱን ጡት መጥባት ባቆመ ጊዜ ሴትዮዋ ወደ ፈርዖን ልጅ መለሰችው ስሙንም “ሙሴ” ብለው ጠሩት።

9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው — illustration 8

አንድ ቀን ሙሴ ባደገ ጊዜ አንድ ግብፃዊ እስራኤላዊ የሆነን ባሪያ ሲመታው አየ ሙሴም እስራኤላዊ ወገኑን ሊያድነው ሞከረ።

9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው — illustration 9

ሙሴ ማንም የማያይ መስሎት ግብፃዊውን ገድሎ ቀበረው። ነገር ግን ሙሴ ያደረገውን አንድ ሰው አይቶታል።

9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው — illustration 10

ሙሴ ያደረገውን ፈርዖን በሰማ ጊዜ ሊገድለው ሞከረ። ሙሴ ግን ከፈርዖን ወታደሮች ነፍሱን ወደሚያድንበት ከግብፅ ወደ ምድረ በዳ ሸሸ።

9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው — illustration 11

ከግብፅ ሩቅ በሆነ ምድረ በዳ ሙሴ የበጐች እረኛ ሆነ። ከዚያም አገር ሚስት አግብቶ ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ።

9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው — illustration 12

አንድ ቀን ሙሴ በጐቹን እየጠበቀ ሳለ እሳት የሚነድበት ቊጥቋጦ ተመለከተ ይሁን እንጂ ቊጥቋጦው አልተቃጠለም፤ ሙሴም በደንብ ለማየት ወደ ቊጥቋጦው ጠጋ አለ። ወደሚቃጠለው ቊጥቋጦ ጠጋ ሲል የእግዚአብሔር ድምፅ “ሙሴ በቅዱስ ስፍራ ቆመሃልና ከእግርህ ጫማህን አውልቅ” አለው።

9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው — illustration 13

እግዚአብሔርም አለ “የሕዝቤን መከራ አይቻለሁና ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ እስራኤልንም ከግብፅ ባርነት ነጻ ታወጣቸዋለህ። ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ተስፋ የሰጠኋቸውን የከነዓንን ምድር እሰጣቸዋለሁ።”

9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው — illustration 14

ሕዝቡ ማንላከህ ብለው ቢጠይቁኝ ምን እላቸዋለሁ ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርምሙሴን “እኔ ያለሁና የምኖር ነኝ ስለዚህ‘ያለና የሚኖር’ ልኮኛልብለህ ንገራቸው” አለው።

9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው — illustration 15

ሙሴ ስለ ፈራ ወደ ፈርዖን መሄድ አልፈለገም። ምክንያቱም የንግግር ችሎታ የለኝም ብሎ በማሰቡ ነበር። ስለዚህም እግዚአብሔር የሙሴን ወንድም አሮንን አብሮት እንዲሄድና ሙሴን እንዲረዳው ላከው። እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን ፈርዖን ሕዝቡን አለቅም በሚል ልቡን ሊያደነድን እንደሚችል አስጠነቀቃቸው።

**የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፅአት 1-4።**

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).