8. እግዚአብሔር ዮሴፍንና ቤተ ሰቡን አዳነ

8. እግዚአብሔር ዮሴፍንና ቤተ ሰቡን አዳነ — illustration 1

ከብዙ ዓመታት በኋላ ያዕቆብ ባረጀ ጊዜ የከብቶቹን መንጋ የሚጠብቁት ወንድሞቹ እንዴት እንዳሉ እንዲያያቸው የሚወደው ልጁን ዮሴፍን ላከው።

8. እግዚአብሔር ዮሴፍንና ቤተ ሰቡን አዳነ — illustration 2

አባታቸው ያዕቆብ ዮሴፍን ከወንድሞቹ ሁሉ አብዝቶ ይወድደው ስለ ነበረና አለቃቸው እንደሚሆን ሕልም አልሞ ስለ ነበር የዮሴፍ ወንድሞች ጠሉት። ዮሴፍም ወደ ወንድሞቹ በመጣ ጊዜ ጠልፈውት ለባሪያ ነጋዴዎች ሸጡት።

8. እግዚአብሔር ዮሴፍንና ቤተ ሰቡን አዳነ — illustration 3

የዮሴፍ ወንድሞች ወደ ቤት ከመመለሳቸው በፊት የዮሴፍን ቀሚስ ቀድደው በፍየል ደም ነከሩት። ከዚያም በደም የተነከረውን የዮሴፍን ቀሚስ ለአባታቸው አሳዩት። እርሱም የዱር አውሬ ዮሴፍን ገድሎታል ሲል አሰበ፤ ያዕቆብም በጣም አዘነ።

8. እግዚአብሔር ዮሴፍንና ቤተ ሰቡን አዳነ — illustration 4

የባሪያ ነጋዴዎቹ ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት። በዚያን ጊዜ ግብፅ በአባይ ወንዝ አጠገብ የምትገኝ ታላቅና ኃያል አገር ነበረች። የባሪያ ነጋዴዎቹ ዮሴፍን ባርያ አድርገው ለሀብታም የመንግሥት ባለ ሥልጣን ሸጡት። ዮሴፍ ጌታውን በደንብ አድርጎ አገለገለው። እግዚአብሔርም ዮሴፍን ባረከው።

8. እግዚአብሔር ዮሴፍንና ቤተ ሰቡን አዳነ — illustration 5

የጌታው ሚስት ከዮሴፍ ጋር ለመተኛት ሞከረች። ዮሴፍ ግን በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት አልሠራም ሲል እምቢ አላት። እሷም ስለ ተናደደችበት በሐሰት ከስሳው ተይዞ ወደ እሥር ቤት ተወሰደ በእሥር ቤትም ቢሆን ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ ስለ ተገኘ እግዚአብሔር ባረከው።

8. እግዚአብሔር ዮሴፍንና ቤተ ሰቡን አዳነ — illustration 6

ምንም እንኳ ዮሴፍ ንጹሕ ሰው ቢሆንም ከሁለት ዓመት በኋላ አሁንም በእሥር ቤት ነበር። አንድ ሌሊት ግብፃውያን ‘ንጉሣችን’ የሚሉት ፈርዖን በጣም የታወከባቸውን ሁለት ሕልሞች አለመ። ከአማካሪዎቹ አንዳቸውም የሕልሙን ትርጕም ሊነግሩት አልቻሉም።

8. እግዚአብሔር ዮሴፍንና ቤተ ሰቡን አዳነ — illustration 7

እግዚአብሔር ለዮሴፍ ሕልም የመተርጐም ችሎታ ሰጥቶት ነበር፤ ስለዚህ ፈርዖን ዮሴፍን ከእሥር ቤት ወደ ራሱ አስመጣው። ዮሴፍ ሕልሙን ተረጐመለትና እንዲህ አለው። “እግዚአብሔር ሰባት የጥጋብ ዓመታትን ይልካል፣ ቀጥሎም ሰባት የረሀብ ዓመታት ይሆናሉ” አለ።

8. እግዚአብሔር ዮሴፍንና ቤተ ሰቡን አዳነ — illustration 8

ፈርዖንም በዮሴፍ በጣም ተገረመ፣ በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ከእርሱ ቀጥሎ ሁለተኛ ባለ ሥልጣን አድርጎ ሾመው።

8. እግዚአብሔር ዮሴፍንና ቤተ ሰቡን አዳነ — illustration 9

ዮሴፍም ሕዝቡን በሰባቱ የመልካም ምርት ዓመታት በርካታ እህል በጎተራው እንዲያከማቹ ነገራቸው። የሰባቱ የረሀብ ዓመታት በመጡ ጊዜ ዮሴፍ ከጎተራው ለሕዝቡ እህል በመሸጡ በቂ የሚበላ ምግብ አገኙ።

8. እግዚአብሔር ዮሴፍንና ቤተ ሰቡን አዳነ — illustration 10

የረሀቡ አስከፊነት በግብፅ ብቻ ሳይሆን፣ ያዕቆብና ቤተ ሰቡ በሚኖሩበት በከነዓን ምድር ደግሞ ነበር።

8. እግዚአብሔር ዮሴፍንና ቤተ ሰቡን አዳነ — illustration 11

ያዕቆብ ልጆቹ እህል እንዲሸምቱ ወደ ግብፅ ላካቸው። የዮሴፍ ወንድሞች ለእህል ሸመታ ሄደው ፊቱ በቆሙ ጊዜ ዮሴፍ መሆኑን አላስተዋሉትም ዮሴፍ ግን አውቋቸዋል።

8. እግዚአብሔር ዮሴፍንና ቤተ ሰቡን አዳነ — illustration 12

ዮሴፍ ወንድሞቹን ከፈተናቸው በኋላ ተለውጠው እንደ ሆነ ለማየት እንዲህ አላቸው፣ “አትፍሩ እኔ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ ለባርነት ስትሸጡኝ ክፉ ልታደርጉብኝ ሞከራችሁ ነገር ግን እግዚአብሔር ክፉውን ለመልካም አደረገው መጥታችሁ በግብፅ ኑሩ እኔም ለእናንተና ለቤተ ሰቦቻችሁ የሚያስፈልጋችሁን አቀርብላችኋለሁ።”

8. እግዚአብሔር ዮሴፍንና ቤተ ሰቡን አዳነ — illustration 13

የዮሴፍ ወንድሞች ወደአገራቸው ተመልሰው ዮሴፍ በሕይወት መኖሩን ለአባታቸውለያዕቆብ በነገሩት ጊዜ ያዕቆብበጣም ደስ አለው።

8. እግዚአብሔር ዮሴፍንና ቤተ ሰቡን አዳነ — illustration 14

ምንም እንኳ ያዕቆብ ሽማግሌ ቢሆንም ከመላው ቤተሰቡ ጋር ወደ ግብፅ ሄዶ በዚያ ኖሩ። ያዕቆብ ከመሞቱ በፊት ልጆቹን እያንዳንዳቸውን ባረካቸው።

8. እግዚአብሔር ዮሴፍንና ቤተ ሰቡን አዳነ — illustration 15

እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባቸው የቃል ኪዳን ተስፋዎች ወደ ይስሐቅ ተላለፉ፤ ከዚያም ወደ ያዕቆብ፣ ቀጥሎም ወደ ዐሥራ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆቹና ቤተ ሰቦቻቸው ተላለፈ። የዐሥራ ሁለቱ ልጆች ዘሮቻቸው ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ሆኑ።

**የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 37-50።**

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).