7. እግዚአብሔር ያዕቆብን ባረከ

7. እግዚአብሔር ያዕቆብን ባረከ — illustration 1

ልጆቹም እንዳደጉ ያዕቆብ ከእናቱ ጋር በቤት መቆየትን ይወድ ነበር። ኤሳው ግን አደን ማደን ይወድ ነበር። ርብቃ ያዕቆብን ትወድደው ነበር፣ ይስሐቅ ግን ኤሳውን ይወድደው ነበር።

7. እግዚአብሔር ያዕቆብን ባረከ — illustration 2

ከዕለታት አንድ ቀን ኤሳው ከአደን ተመልሶ ሲመጣ በጣም ተርቦ ነበር። ኤሳው ያዕቆብን “እባክህ ካዘጋጀኸው ምግብ ትንሽ ስጠኝ” አለው። ያዕቆብም በመጀመሪያ የብኩርናህን መብት ስጠኝ ሲል መለሰለት። ስለዚህም ኤሳው የብኩርናውን መብት ለያዕቆብ ሰጠው ከዚያም ያዕቆብ ከሠራው ምግብ ሰጠው።

7. እግዚአብሔር ያዕቆብን ባረከ — illustration 3

ይስሐቅ በረከቱን ለኤሳው ሊሰጠው ፈለገ።ነገር ግንይህን ከማድረጉበፊት ርብቃና ያዕቆብ ይስሐቅን አታለሉት። ያዕቆብ ኤሳውንመስሎ ወደ ይስሐቅ ቀረበ። ይስሐቅ አርጅቶነበር ማየትም አይችልም ነበር። ስለዚህም ያዕቆብ የኤሳውን ልብሶችለብሶ የፍየልለምድ በአንገቱናበእጁ አድርጎ ወደ ይስሐቅ በመቅረብ ይስሐቅን አታለለው።

7. እግዚአብሔር ያዕቆብን ባረከ — illustration 4

ያዕቆብ ወደ ኤሳው መጣና እንዲህ አለው፣ “እኔ ኤሳው ነኝ መጥቻለሁና ልትባርከኝ ትችላለህ” ይስሐቅ የፍየሉን ፀጉር ዳሰሰና የልብሱንም ጠረን አሽትቶ ኤሳው እንደ ሆነ አሰበና ባረከው።

7. እግዚአብሔር ያዕቆብን ባረከ — illustration 5

ያዕቆብ የብኵርና መብቱንና በረከቱን አታልሎ ስለ ወሰደበት ኤሳው ያዕቆብን ጠላው አባታቸው ከሞተ በኋላ ሊገድለውም አሰበ።

7. እግዚአብሔር ያዕቆብን ባረከ — illustration 6

ነገር ግን ርብቃ የኤሳውን እቅድ ሰማች። ስለዚህም እሷና ይስሐቅ ከዘመዶቹ ጋር እንዲኖር ወደ ሩቅ አገር ያዕቆብን ሰደዱት።

7. እግዚአብሔር ያዕቆብን ባረከ — illustration 7

ያዕቆብ ለረዥም ዓመታት ከርብቃ ዘመዶች ጋር ኖረ። በዚያም ጊዜ ትዳር መስርቶ 12 ወንዶች ልጆችና 1 ሴት ልጅ ወለደ። እግዚአብሔርም በጣም አበለጸገው።

7. እግዚአብሔር ያዕቆብን ባረከ — illustration 8

በከነዓን ከኖረበት ከሃያ (20) ዓመታት በኋላ ያዕቆብ ከቤተ ሰቡ፣ ከሠራተኞቹና ከመንጋው ሁሉ ጋር ወደ ከነዓን ምድር ለመመለስ ወሰነ።

7. እግዚአብሔር ያዕቆብን ባረከ — illustration 9

ኤሳው አሁንም ሊገድለኝ ያስብ ይሆናል ብሎ በልቡ ስላሰበ ያዕቆብ ፈራ። ስለዚህም የእጅ መንሻ እንዲሆነው የብዙ ከብቶች መንጋ ስጦታ አድርጎ ለኤሳው ላከለት። ከብቶቹን ያመጡለት የያዕቆብ አገልጋዮች ኤሳውን “አገልጋይህ ያዕቆብ እነዚህን ከብቶች ልኮልሃል እርሱም በቅርቡ ይመጣል” አሉት።

7. እግዚአብሔር ያዕቆብን ባረከ — illustration 10

ኤሳው ግን ቀድሞውኑ ያዕቆብን ይቅር ብሎት ስለ ነበር ዳግም ለመገናኘት ደስተኞች ነበሩ። ያዕቆብ በከነዓን ምድር በሰላም ኖረ፤ ከዚያም ይስሐቅ ሞተ ያዕቆብና ኤሳው ቀበሩት እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባለት የቃል ኪዳኑ ተስፋ አሁን ከይስሐቅ ወደ ያዕቆብ ተላለፈ።

**የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 25፡27-33፡20።**

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).