6. እግዚአብሔር ለይስሐቅ ሚስት አዘጋጀለት

6. እግዚአብሔር ለይስሐቅ ሚስት አዘጋጀለት — illustration 1

አብርሃም በጣም ባረጀ ጊዜ ይስሐቅ ዕድሜው ለአቅመ አዳም ደረሰ። ስለዚህ አብርሃም ከአገልጋዮቹ አንዱን ወደ ዘመዶቹ ምድር ለልጁ ለይስሐቅ ሚስት እንዲያመጣለት ላከው።

6. እግዚአብሔር ለይስሐቅ ሚስት አዘጋጀለት — illustration 2

የአብርሃም ዘመዶች ወደሚኖሩበት ምድር ከረጅም ጒዞ በኋላ ደረሰ። እግዚአብሔርም የተላከውን የአብርሃምን አገልጋይ ወደ ርብቃ መራው። ርብቃ የአብርሃም ወንድም የልጅ ልጅ ነበረች።

6. እግዚአብሔር ለይስሐቅ ሚስት አዘጋጀለት — illustration 3

ርብቃ ቤተ ሰቦቿን ትታ ከአገልጋዩ ጋር ወደ ይስሐቅ ቤት ለመሄድ ተስማማች። እንደ ደረሰችም ይስሐቅ አገባት።

6. እግዚአብሔር ለይስሐቅ ሚስት አዘጋጀለት — illustration 4

ከረጅም ጊዜበኋላ አብርሃምሞተና እግዚአብሔርከአብርሃም ጋርየገባው የተስፋ ቃል ኪዳን ሁሉ ወደ ይስሐቅተላለፈ። እግዚአብሔርለአብርሃም ሊቈጠር የማይችል ዘር እንደሚኖረው ተስፋ ሰጥቶት ነበር። ይሁን እንጂ የይስሐቅ ሚስት ርብቃ ልጆች ልትወልድ አልቻለችም።

6. እግዚአብሔር ለይስሐቅ ሚስት አዘጋጀለት — illustration 5

ይስሐቅ ለርብቃ ጸለየላትና እግዚአብሔር መንታ ልጆችን እንድታረግዝ ፍቃዱ ሆነ። ሁለቱ ልጆች በርብቃ ማኅፀን ሳሉ እርስ በርሳቸው ይታገሉ ነበር። ርብቃም በማኅፀንዋ እየሆነ ያለው ምን እንደሆነ እግዚአብሔርን ጠየቀች።

6. እግዚአብሔር ለይስሐቅ ሚስት አዘጋጀለት — illustration 6

እግዚአብሔርም ርብቃን አላት፣ “በማኅፀንሽ ካሉት ከሁለቱ ልጆች ሁለት ሕዝቦች ይወጣሉ እነርሱም እርስ በርሳቸው ይታገላሉ ታላቁም ታናሹን ያገለግላል” አላት።

6. እግዚአብሔር ለይስሐቅ ሚስት አዘጋጀለት — illustration 7

የርብቃ ልጆች በተወለዱ ጊዜ ታላቁ ልጅ ቀይና ፀጉራም ሆኖ ወጣ ‘ኤሳው’ ሲሉትም ስም አወጡለት፤ ታናሹም ልጅ የኤሳውን ተረከዝ ይዞ ወጣ ስሙንም ‘ያዕቆብ’ ሲሉ አወጡለት።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 24፡1-25፤ 26።

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).