12. የእስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት

12. የእስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት — illustration 1

እስራኤላውያን ከግብፅ በመውጣታቸው በጣም ደስ አላቸው። ከእንግዲህ ባሪያዎች አይደሉም፣ ወደ ተስፋዪቱ ምድርም በመጓዝ ላይ ነበሩ! ግብፃውያን ለእስራኤላውያን ወርቅና ብር ሌሎችም የከበሩ ነገሮች ሳይቀሩ የጠየቁትን ማንኛውንም ነገር ሰጡአቸውና ከግብፅ ሲወጡ ከሌሎች ብሔሮች የሆኑ አንዳንድ ሰዎች በእግዚአብሔር አምነው ከእስራኤላውያን ጋር ሄዱ።

12. የእስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት — illustration 2

እግዚአብሔር በፊታቸው በሚሄድ ቀን ረጅም በሆነ የደመና ዓምድ፣ ማታም ረጅም በሆነ የእሳት ዓምድ መራቸው። እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከእነርሱ ጋር ነበርና ሲጓዙ መራቸው። ማድረግ ያለባቸው ነገር ቢኖር እርሱን መከተል ብቻ ነበር።

12. የእስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት — illustration 3

ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ ፈርዖንና ሕዝቡ ዐሳባቸውን ለወጡና እስራኤላውያን እንደ ገና የእነርሱ ባሪያዎች እንዲሆኑ ፈለጉ። እግዚአብሔር ብቸኛው እውነተኛ አምላክ መሆኑን ሕዝቡ እንዲያዩ፣ እንዲሁም እርሱ፣ ያሕዌ፣ ከፈርዖንና ከአማልክቱ የበለጠ ኃያል እንደ ሆነ ይረዱ ዘንድ ፈርዖንን ዐሳበ ግትር አደረገው።

12. የእስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት — illustration 4

ስለዚህ ፈርዖንና ጦር ሠራዊቱ እንደ ገና ባሪያዎቻቸው ሊያደርጉአቸው እስራኤላውያንን አሳደዱአቸው። እስራኤላውያን የግብፅ ጦር ሠራዊት ሲመጣ ባዩ ጊዜ፣ በፈርዖን ጦር ሠራዊትና በቀይ ባሕር መካከል እንደ ተጠመዱ ዐወቁ። በጣም ፈርተው ስለ ነበር፣ “ከግብፅ ለምን ወጣን? መሞታችን ነው!” ብለው ጮኹ።

12. የእስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት — illustration 5

ሙሴ እስራኤላውያንን፣ “አትፍሩ! ዛሬ እግዚአብሔር ይዋጋላችሁና ያድናችኋል” ብሎ ነገራቸው። ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ወደ ቀይ ባሕር እንዲንቀሳቀሱ ለሕዝቡ ንገራቸው” ብሎ ለሙሴ ነገረው። ከዚያም እግዚአብሔር ግብፃውያን እስራኤላውያንን ማየት እንዳይችሉ የደመናውን ዓምድ በእስራኤላውያንና በግብፃውያን መካከል አደረገው።

12. የእስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት — illustration 6

እግዚአብሔር ለሙሴ በባሕሩ ላይ እጁን እንዲዘረጋና ውሃውን እንዲከፍለው ነገረው። ከዚያም እግዚአብሔር በባሕሩ መተላለፊያ መንገድ ይኖር ዘንድ ውሃውን ነፋስ ወደ ግራና ወደ ቀኝ እንዲያንቀሳቅሰው አደረገ።

12. የእስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት — illustration 7

እግዚአብሔር ለሙሴ በባሕሩ ላይ እጁን እንዲዘረጋና ውሃውን እንዲከፍለው ነገረው። ከዚያም እግዚአብሔር በባሕሩ መተላለፊያ መንገድ ይኖር ዘንድ ውሃውን ነፋስ ወደ ግራና ወደ ቀኝ እንዲያንቀሳቅሰው አደረገ።

12. የእስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት — illustration 8

እስራኤላውያን ውሃው በግራና በቀኛቸው ግድግዳ ሆኖላቸው በባሕሩ በደረቅ መሬት ላይ ተጓዙ።

12. የእስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት — illustration 9

ከዚያም እግዚአብሔር ግብፃውያኑ እስራኤላውያን ማምለጣቸውን ያዩ ዘንድ ደመናውን ከመንገዱ ወደ ላይ አንቀሳቀሰው። ግብፃውያን ከኋላቸው ሆነው ሊያሳድዱአቸው ወሰኑ።

12. የእስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት — illustration 10

ስለዚህ በባሕሩ መንገድ እስራኤላውያንን ተከተሉአቸው፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ግብፃውያን እንዲጨነቁና ሰረገሎቻቸውም እንዲታሰሩ አደረገ። “ሽሹ! እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን እየተዋጋላቸው ነው!” ብለው ጮኹ።

12. የእስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት — illustration 11

እስራኤላውያን ባሕሩን በደኅና ከተሻገሩ በኋላ፣ እግዚአብሔር እንደ ገና እጁን እንዲዘረጋ ለሙሴ ነገረው። እርሱም በታዘዘ ጊዜ፣ ውሃው በግብፃውያን ሠራዊት ላይ ተመለሰና እንደ መጀመሪያው ሆነ። መላው የግብፃውያን ጦር ሠራዊት ሰጠመ።

12. የእስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት — illustration 12

እስራኤላውያን ግብፃውያን እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ በእግዚአብሔር አመኑ ሙሴም የእግዚአብሔር ነቢይ መሆኑን አመኑ።

12. የእስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት — illustration 13

ደግሞም እስራኤላውያን እግዚአብሔር ከሞትና ከባርነት ስለ አዳናቸው በብዙ ደስታ ደስ አላቸው! አሁን እግዚአብሔርን ለማገልገል ነጻ ሆኑ። እስራኤላውያን እርሱ ከግብፃውያን ጦር ሠራዊት ስለ አዳናቸው ዐዲሱን ነጻነታቸውን ለማክበርና እግዚአብሔርን ለማመስገን ብዙ መዝሙሮችን ዘመሩ።

12. የእስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት — illustration 14

እንዴት እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ድልን እንደ ሰጣቸውና ባሪያዎች ከመሆን እንዳዳናቸው ያስታውሱ ዘንድ በያመቱ ፋሲካን እንዲያከብሩ እስራኤላውያንን አዘዛቸው። ፍጹም የሆነ ጠቦት አርደው ካልቦካ ቂጣ ጋር በመብላት ተደሰቱ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘጸአት 12፡33-15፡21።

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).