13. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን

13. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን — illustration 1

እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በቀይ ባሕር በኩል ከመራቸው በኋላ፣ በምድረ በዳ በኩል ሲና ተብሎ ወደሚጠራ ተራራ ወሰዳቸው። ይህም ሙሴ የሚቃጠለውን ቊጥቋጦ ያየበት ተራራ ነው። ሕዝቡ በተራራው ሥር ድንኳኖቻቸውን ተከሉ።

13. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን — illustration 2

እግዚአብሔር፣ “ለእኔ ብትታዘዙና ቃል ኪዳኔን ብትጠብቁ፣ የከበረ ርስት፣ የንጉሥ ካህናት፣ እንዲሁም ቅዱስ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ” ብሎ ለሙሴና ለእስራኤል ሕዝብ ተናገረ።

13. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን — illustration 3

ሕዝቡ በመንፈሳዊ በኩል ራሳቸውን ካዘጋጁ ከሦስት ቀን በኋላ፣ እግዚአብሔር በነጐድጓድ፣ በመብረቅ፣ በጢስ እንዲሁም ከፍ ባለ የመለከት ድምፅ በሲና ተራራ ላይ ወረደ። ወደ ተራራው እንዲወጣ የተፈቀደው ለሙሴ ብቻ ነበር።

13. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን — illustration 4

ከዚያም እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ሰጣቸውና እንዲህ አለ፣ “እኔ ከግብፅ ባርነት ያዳንኳችሁ፣ አምላካችሁ፣ ያህዌ ነኝ። ሌሎችን አማልክት አታምልኩ።”

13. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን — illustration 5

“ጣዖታትን አትሥራ አታምልካቸውም፣ ምክንያቱም እኔ፣ ያህዌ ቀናተኛ አምላከ ነኝ። ስሜን በከንቱ አትጥራ፣ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ ዐስብ። ይኸውም ሥራህን ሁሉ በስድስት ቀን ሥራ፣ ምክንያቱም ሰባተኛው ቀን የምታርፍበትና እኔን የምታስታውስበት ዕለት ነው።”

13. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን — illustration 6

“አባትህንና እናትህን አክብር። አትግደል። አታመንዝር። አትስረቅ። አትዋሽ። የባልንጀራህን ሚስት፣ ቤቱን፣ ወይም የእርሱ የሆነውን ማንኛውም ነገር ለመውሰድ አትመኝ።”

13. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን — illustration 7

ከዚያም እግዚአብሔር እነዚህን ዐሥር ትእዛዛት በሁለት ጠፍጣፋ ድንጋዮች ላይ ጽፎ ለሙሴ ሰጠው። ደግሞ እግዚአብሔር የሚከተሉአቸው ሌሎች ብዙ ሕግጋትንና ደንቦችን ሰጣቸው። ሕዝቡ እነዚህን ሕግጋት ከፈጸሙ እግዚአብሔር እንደሚባርካቸውና እንደሚጠብቃቸው ተስፋ ሰጠ። ሕግጋቱን ካልፈጸሙ ግን እግዚአብሔር ይቀጣቸዋል።

13. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን — illustration 8

ደግሞም እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን እንዲሠሩት ስለሚፈልገው ድንኳን መግለጫ ሰጣቸው። እርሱ የመገናኛው ድንኳ ተብሎ ይጠራ ነበር፣ በትልቅ መጋረጃ የተከፈሉ ሁለት ክፍሎችም ነበሩት። እግዚአብሔር በዚያ ይኖር ስለ ነበረ፣ ከመጋረጃ በስተጀርባ ወዳለው ክፍል እንዲገባ የተፈቀደለት ሊቀ ካህን ብቻ ነበር።

13. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን — illustration 9

የእግዚአብሔርን ሕግ ያልፈጸመ ማንኛውም ሰው በመገናኛው ድንኳ ፊት ለፊት ወዳለው መሠዊያ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት የሚሆን እንስሳ ማምጣት ይችል ነበር። ካህኑ እንስሳውን ያርድና በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው ነበር። የተሠዋው እንስሳ ደም የሰውዬውን ኃጢአት ይሸፍንና ያንን ሰው በእግዚአብሔር ፊት ያነጻው ነበር። እግዚአብሔር ካህናቱ ይሆኑ ዘንድ የሙሴን ወንድም አሮንን፣ እንዲሁም የአሮንን ዝርያዎች መረጠ።

13. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን — illustration 10

ሕዝቡ ሁላቸውም እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዛት ለመፈጸም፣ እግዚአብሔርን ብቻ ለማምለክ፣ እንዲሁም የተለዩ ሕዝቡ ለመሆን ተስማሙ። ነገር ግን ለእግዚአብሔር ለመታዘዝ ቃል ከገቡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ክፉኛ ኃጢአት ሠሩ።

13. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን — illustration 11

ሙሴ ለብዙ ቀናት በሲና ተራራ ጫፍ ላይ ሆኖ ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገር ነበር። ሕዝቡ እርሱ እስኪመለስ ድረስ መጠባበቅ ሰለቻቸው። ስለዚህ ወደ አሮን ወርቅ አመጡና ጣዖት እንዲሠራላቸው ጠየቁት!

13. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን — illustration 12

አሮን በጥጃ ቅርፅ የወርቅ ጣዖት ሠራ። ሕዝቡ ከቊጥጥር ውጭ በሆነ ሁኔታ ጣዖቱን ማምለክ ጀመሩ፣ መሥዋዕትም ሠዉለት! በኃጢአታቸው ምክንያት እግዚአብሔር በጣም ተቈጣቸው፣ ሊያጠፋቸውም ዐቀደ። ነገር ግን ሙሴ ጸለየላቸው፣ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰማ እነርሱን አላጠፋቸውም።

13. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን — illustration 13

ሙሴ ከተራራው በወረደና ጣዖቱን ባየ ጊዜ፣ በጣም ተቈጥቶ እግዚአብሔር ዐሥሩን ትእዛዛት የጻፈባቸውን ድንጋዮች ሰባበረ።

13. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን — illustration 14

ከዚያም ሙሴ ጣዖቱን ፈጨው፣ በውሃውም ላይ በተነው፣ ለሕዝቡም አጠጣቸው። እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ መቅሠፍት ላከና ብዙዎቻቸው ሞቱ።

13. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን — illustration 15

ሙሴ እንደ ገና ተራራው ላይ ወጣና እግዚአብሔር ሕዝቡን ይቅር እንዲላቸው ጸለየ። እግዚአብሔር ሙሴን ሰማውና ይቅር አላቸው። ሙሴ የሰባበራቸውን ለመተካት በዐዲስ ጠፍጣፋ ድንጋዮች ላይ ዐሥሩን ትእዛዛት ጻፈ። ከዚያም እግዚአብሔር እስራኤላውያን ከሲና ተራራ ወደ ተስፋዪቱ ምድር መራቸው።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘጸአት 19-34።

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).