27.የደጉ ሳምራዊ ታሪክ

27.የደጉ ሳምራዊ ታሪክ — illustration 1

አንድ ቀን አንድ የአይሁድ ሕግ ዐዋቂ ሊፈትነው ወደ ኢየሱስ መጣ፣ “መምህር ሆይ፣ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ?” አለው። ኢየሱስ፣ “በእግዚአብሔር ሕግ የተጻፈው ምንድን ነው?” ብሎ መለሰለት።

27.የደጉ ሳምራዊ ታሪክ — illustration 2

ሕግ ዐዋቂው የእግዚአብሔርሕግ፣ “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም ዐሳብህም ውደድ። ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ” ይላል ብሎ መለሰ። ኢየሱስ፣ “ትክክል ነህ! ይህን አድርግ በሕይወትም ትኖራለህ” አለው።

27.የደጉ ሳምራዊ ታሪክ — illustration 3

ነገር ግን ሕግ ዐዋቂው ጻድቅ መሆኑን ለማረጋገጥ ፈለገ፣ ስለዚህ፣ “ባልንጀራዬ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀ።

27.የደጉ ሳምራዊ ታሪክ — illustration 4

ኢየሱስ ታሪክ በመናገር ለሕግ ዐዋቂው መለሰለት። “ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ይጓዝ የነበረ አንድ አይሁዳዊ ነበረ።”

27.የደጉ ሳምራዊ ታሪክ — illustration 5

“ሰውዬው በመጓዝ ላይ እያለ ወንበዴዎች ያዙት። የነበረውን ነገር ሁሉ ወሰዱበትና እስኪሞት ድረስ ደበደቡት። ከዚያም ሄዱ።”

27.የደጉ ሳምራዊ ታሪክ — illustration 6

ከዚያ በኋላ ወዲያውኑ አንድ አይሁዳዊ ካህን በዚያ መንገድ ይጓዝ ነበር። ይህ የሃይማኖት መሪ የተዘረፈውንና የተደበደበውን ሰው ባየ ጊዜ ወደ መንገዱ ሌላኛ ጎን ሄደ፣ ርዳታ የፈለገውን ሰው ቸል አለውና ጕዞውን ቀጠለ።"

27.የደጉ ሳምራዊ ታሪክ — illustration 7

ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ፣አንድ ሌዋዊ መጣ።( ሌዋውያን በቤተ መቅደስ ካህናቱን የሚረዱ የአይሁድ ነገድ ነበሩ።) ሌዋዊውም ደግሞ ወደ መንገዱ ሌላኛ ጎን ተሻገረና የተዘረፈውንና የተደበደበውን ሰው በቸልታ አለፈው።"

27.የደጉ ሳምራዊ ታሪክ — illustration 8

በዚያ መንገድ የወረደው የሚቀጥለው ሰው ሳምራዊ ነበር።(ሳምራውያን የሌሎች አገሮች ሰዎችን ያገቡ የአይሁድ ዝርያዎች ነበሩ።ሳምራውያንና አይሁዳውያን እርስ በርስ ይጠላሉ ነበር።) ነገር ግን ሳምራዊው አይሁዳዊውን ባየ ጊዜ በጣም አድርጎ ራራለት። ስለዚህ ተንከባከበውና ቊስሉን አሰረለት።"

27.የደጉ ሳምራዊ ታሪክ — illustration 9

“ከዚያ በኋላ ሳምራዊው ሰውዬውን አንሥቶ በራሱ አህያ ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማደሪያ ወሰደው ተንከባከበውም።”

27.የደጉ ሳምራዊ ታሪክ — illustration 10

“በማግሥቱም ሳምራዊው ጕዞውን መቀጠል አስፈለገው። ለእንግዶች ማረፊያው ባለቤት ጥቂት ገንዘብ ሰጠውና፣”ተንከባከበው፣ ከዚህ ሌላ ገንዘብ የምታወጣ ከሆነ በምመለስበት ጊዜ እከፍልሃለሁ አለው።"

27.የደጉ ሳምራዊ ታሪክ — illustration 11

ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ሕግ ዐዋቂውን፣ “ምን ታስባለህ? ለተዘረፈውና ለተደበደበው ሰው ባልንጀራው ከሦስቱ ሰዎች የትኛው ነበር?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም፣ “ምሕረት ያደረገለት ነበር” ብሎ መለሰለት። ኢየሱስ፣ “አንተም ሄደህ እንደዚሁ አድርግ” ብሎ ነገረው።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከሉቃስ 10፡25-37።

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).