28. ባለ ጠጋው ወጣት

28. ባለ ጠጋው ወጣት — illustration 1

አንድ ቀንአንድ ባለጠጋወጣት ወደ ኢየሱስ መጣና፣ “ቸር መምህር፣ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ?” ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስ፣ “ስለ ምን ‘ቸር’ ትለኛለህ? ቸርአንድ ብቻአለ፣ እርሱም እግዚአብሔር ነው።ነገር ግንአንተ የዘላለም ሕይወት እንዲኖርህ ከፈለግህ ለእግዚአብሔር ሕግታዘዝ” አለው።

28. ባለ ጠጋው ወጣት — illustration 2

“የትኞቹን ልታዘዝ?” ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፣ “አትግደል። አታመንዝር። አትስረቅ። አትዋሽ። አባትህንና እናትህን አክብር፣ ባልጀራህንምእንደ ራስህ ውደድ።”

28. ባለ ጠጋው ወጣት — illustration 3

ነገር ግን ወጣቱ፣ “ከልጅነቴጀምሮ እነዚህንሕጎች ሁሉ ፈጽሜአለሁ። ለዘላለም ለመኖርሌላስ ምን ማድረግ ያስፈልገኛል?” አለ። ኢየሱስ ዐየውና ወደደው።

28. ባለ ጠጋው ወጣት — illustration 4

ኢየሱስ፣ “ፍጹም ለመሆን ብትፈልግ፣ ያለህን ንብረት ሁሉሽጥና ገንዘቡን ለድሆች ስጥ፣ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ። ከዚያም በኋላ ናና ተከተለኝ” ብሎመለሰለት።

28. ባለ ጠጋው ወጣት — illustration 5

ወጣቱ፣ ኢየሱስ የተናገረውን በሰማ ጊዜ፣ በጣም ባለ ጠጋ ነበርና ያለውን ነገር ሁሉ መስጠት ስላልፈለገ በጣም ዐዘነ። ከኢየሱስ ፊቱን አዞረና ሄደ።

28. ባለ ጠጋው ወጣት — illustration 6

በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፣ “ለባለ ጠጎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እጅግ አስቸጋሪ ነው! አዎ፣ ባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል።”

28. ባለ ጠጋው ወጣት — illustration 7

ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ የተናገረውን በሰሙ ጊዜ ደነገጡና፣ “ታዲያ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ።

28. ባለ ጠጋው ወጣት — illustration 8

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ተመለከተና፣ “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል” አለ።

28. ባለ ጠጋው ወጣት — illustration 9

ጴጥሮስ ኢየሱስን፣ “እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ። ዋጋችን ምን ይሆን?” አለው።

28. ባለ ጠጋው ወጣት — illustration 10

ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፣ “ስለ እኔ ቤቶችን፣ ወንድሞችን፣ እኅቶችን፣ አባትን፣ እናትን ወይም ንብረትን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል። ነገር ግን ፊተኞች የሆኑ ብዙዎች ኋለኞች፣ ኋለኞችም የሆኑ ብዙዎች ፊተኞች ይሆናሉ።”

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 19፡16-30፤ ማርቆስ 10፡17-31፤ ሉቃስ 18፡18-30።

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).