29. የምሕረት የለሹ ባሪያ ታሪክ

29. የምሕረት የለሹ ባሪያ ታሪክ — illustration 1

አንድ ቀን ጴጥሮስ ኢየሱስን፣ “መምህር ሆይ፣ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው? እስከ ሰባት ጊዜ ነውን?” ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስ፣ “ሰባት ጊዜ አይደለም፣ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ” አለው። ኢየሱስ ይህን ሲል ሁልጊዜ ይቅር ማለት አለብን ማለቱ ነው። ከዚያም ኢየሱስ ይህን ታሪክ ተናገረ።

29. የምሕረት የለሹ ባሪያ ታሪክ — illustration 2

ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት ባሮቹን ሊቈጣጠር የፈለገን ንጉሥ ትመስላለች። ከባሮቹ አንዱ የ10,000 መክሊት የሚያክል ከፍተኛ ዕዳ ነበረበት።”

29. የምሕረት የለሹ ባሪያ ታሪክ — illustration 3

ባሪያው ዕዳን መክፈል ስላልቻለ፣ ንጉሡ፣ “ዕዳውን ይከፍል ዘንድ ይህን ሰውና ቤተ ሰቡን ሽጡአቸው” አለው።

29. የምሕረት የለሹ ባሪያ ታሪክ — illustration 4

“ባሪያው በንጉሡ ፊት በጉልበቱ ወደቀና፣ ‘እባክህን ታገሠኝ፣ ያለብኝን ዕዳ ሁሉ እከፍልሃለሁ’ አለው። ንጉሡ ለባሪያው አዘነለት፣ ዕዳውንም ሁሉ ሰረዘለትና እንዲሄድ ለቀቀው።”

29. የምሕረት የለሹ ባሪያ ታሪክ — illustration 5

“ነገር ግን ባሪያው ከንጉሡ ዘንድ በወጣ ጊዜ፣ የአራት ወር ደመወዝ የሚሆን ዕዳ ያለበትን ባልንጀሮቹ ከሆኑት ባሪያዎች አንዱን አገኘ። ባሪያው ባልንጀራው የሆነውን ባሪያ ያዘውና፣ ‘ዕዳህን ክፈለኝ!’” አለው።

29. የምሕረት የለሹ ባሪያ ታሪክ — illustration 6

“ባልንጀራው ባሪያ በጉልበቱ ወድቆ፣ ‘እባክህን ታገሠኝ፣ ያለብኝን ዕዳ ሁሉ እከፍልሃለሁ’ አለው። ነገር ግን በዚህ ፈንታ ያ ባሪያ ባልንጀራ ባሪያውን ዕዳውን እስኪከፍለው ድረስ በወኅኒ ጣለው።”

29. የምሕረት የለሹ ባሪያ ታሪክ — illustration 7

“ሌሎች ባሮችም የሆነውን ነገር ዐይተው እጅግ ተረበሹ። ወደ ንጉሡ ሄደውም የሆነውን ነገር ሁሉ ነገሩት።”

29. የምሕረት የለሹ ባሪያ ታሪክ — illustration 8

“ንጉሡ ባሪያውን ጠራና፣ ‘አንተ ክፉ ባሪያ! ስለ ለመንኸኝ ዕዳህን ተውሁልህ። አንተም ይህንኑ ማድረግ ይገባህ ነበር’ አለው። ንጉሡ በጣም ተቈጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍል ድረስ ክፉውን ባሪያ በወኅኒ ጣለው።”

29. የምሕረት የለሹ ባሪያ ታሪክ — illustration 9

ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ይቅር ካላለ፣ እንዲሁ ደግሞ የሰማይ አባቴ ያደርግባችኋል።”

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 18፡21-35።

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).