30. ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን መገበ

30. ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን መገበ — illustration 1

ኢየሱስ በተለያዩ ብዙ መንደሮች እንዲሰብኩና ሰዎችን እንዲያስተምሩ ሐዋርያቱን ላከ። እነርሱ ኢየሱስ ወደ ነበረበት በተመለሱጊዜ፣ ያደረጉትንነገር ነገሩት።ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ሐይቁን ተሻግረውጸጥታ ወዳለበት ቦታ አብረውት እንዲሄዱናጥቂት እንዲያርፉ ጋበዛቸው። ስለዚህጀልባ ውስጥ ገቡና ሐይቁን ተሻገሩ።

30. ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን መገበ — illustration 2

ነገር ግን በጀልባውሲሄዱ ኢየሱስንና ደቀ መዛሙርቱን ያዩአቸው ብዙሰዎች ነበሩ። እነዚህሰዎች ሊቀድሙአቸው በባሕሩዳርቻ ሮጡ። ስለዚህ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ማዶ በደረሱጊዜ፣ በጣም ብዙሰዎች አስቀድመውበዚያ ተገኝተው ይጠባበቁአቸው ነበር።

30. ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን መገበ — illustration 3

ሕዝቡ ሴቶችና ልጆች ሳይቈጠሩ ከ5000 በላይ ወንዶች ነበሩ። ኢየሱስ ለሕዝቡ እጅግ አዘነላቸው። ለኢየሱስ እነዚህ ሕዝብ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ነበሩ። ስለዚህ አስተማራቸውና በመካከላቸው የነበሩትን በሽተኞች ፈወሳቸው።

30. ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን መገበ — illustration 4

በዚያ ምሽት ደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብለው ነገሩት፣ “ጊዜው መሽቶአልና በአቅራቢያው ከተሞች የሉም። የሚበሉትን ነገር ይገዙ ዘንድ ሕዝቡን አሰናብታቸው።”

30. ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን መገበ — illustration 5

ኢየሱስ ግን ደቀ መዛሙርቱን፣ “የሚበሉትን እናንተ ስጡአቸው!” አላቸው። እነርሱም፣“ይህን ማድረግ እንዴት እንችላለን? ያለን አምስት እንጀራናሁለት ዓሣ ብቻ ነው”ብለው መለሱለት።

30. ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን መገበ — illustration 6

ሃምሳ ሃምሳ ሆነው ሣሩ ላይ እንዲቀመጡ ለሕዝቡ ይነግሩ ዘንድ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው።

30. ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን መገበ — illustration 7

ከዚያም ኢየሱስ አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ተመለከተ፣ ስለ ምግቡም እግዚአብሔርን አመሰገነ።

30. ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን መገበ — illustration 8

ከዚያም ኢየሱስ እንጀራውንና ዓሣውን ቈረሰ። ለሕዝቡ እንዲያቀርቡም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው። ደቀ መዛሙርቱ ምግቡን ማደላቸውን ቀጠሉ፣ ከቶም አላለቀም! ሕዝቡ ሁሉ በልተው ጠገቡ።

30. ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን መገበ — illustration 9

ከዚያ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ቊርስራሹን ምግብ ሰበሰቡ፣ እርሱም ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ ነበር! ምግቡ ሁሉ የመጣው ከአምስቱ እንጀራና ከሁለቱ ዓሣ ነበር።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 14፡13-21፤ ማርቆስ 6፡31-44፤ ሉቃስ 9፡10-17፤ ዮሐንስ 6፡5-15።

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).