31. ኢየሱስ በውሃ ላይ ተራመደ

31. ኢየሱስ በውሃ ላይ ተራመደ — illustration 1

ከዚያም ኢየሱስ ሕዝቡን እያሰናበተ እያለ ጀልባ ውስጥ ገብተው እየቀዘፉ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው። ኢየሱስ ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ። በዚያ ኢየሱስ ብቻውን ነበር፣ እስከ እኩለ ሌሊትም ጸለየ።

31. ኢየሱስ በውሃ ላይ ተራመደ — illustration 2

በዚሁ ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱ ጀልባቸውን እየቀዘፉ ነበር፣ በእኩለ ሌሊት የደረሱት ወደ ሐይቁ አጋማሽ ብቻ ነበር። ነፋሱ በእነርሱ ላይ በኃይል ይነፍስ ስለ ነበር የሚቀዝፉት በጣም በችግር ነበር።

31. ኢየሱስ በውሃ ላይ ተራመደ — illustration 3

በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መጸለዩን ጨረሰና ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሄደ። በውሃው ላይ እየተራመደ ሐይቁን አቋርጦ ወደ ጀልባቸው ሄደ!

31. ኢየሱስ በውሃ ላይ ተራመደ — illustration 4

ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን ባዩ ጊዜ በጣም ፈሩ፣ ምክንያቱም ምትሐት ያዩ መሰላቸው፣ ኢየሱስ የፈሩ መሆናቸውን ዐወቀ፣ ስለዚህ ወደ እነርሱ ተጣራና፣ “አትፍሩ። እኔ ነኝ!” አላቸው።

31. ኢየሱስ በውሃ ላይ ተራመደ — illustration 5

በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን፣ “መምህር ሆይ፣ አንተስ ከሆንክ በውሃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዝ” አለው። ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ “ና!” አለው።

31. ኢየሱስ በውሃ ላይ ተራመደ — illustration 6

ስለዚህ ጴጥሮስ ከጀልባው ወጣና በውሃው ላይ ወደ ኢየሱስ መራመድ ጀመረ። ነገር ግን አጭር ርቀት ከተራመደ በኋላ ዓይኖቹን ከኢየሱስ አዞረና ማዕበሉን ያይ ብርቱው ነፋስም ይሰማው ጀመር።

31. ኢየሱስ በውሃ ላይ ተራመደ — illustration 7

በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ፈራና በውሃው መስጠም ጀመረ። “መምህር ሆይ፣ አድነኝ!” ብሎ ጮኸ። ኢየሱስ ወዲያው እጆቹን ዘረጋና ያዘው። ከዚያም ጴጥሮስን፣ “አንተ እምነት የጎደለህ፣ ለምን ተጠራጠርህ?” አለው።

31. ኢየሱስ በውሃ ላይ ተራመደ — illustration 8

ጴጥሮስና ኢየሱስ ወደ ጀልባው በገቡ ጊዜ፣ ነፋሱ መንፈሱን ወዲያውኑ አቆመና ጸጥ አለ። ደቀ መዛሙርቱ ተደነቁ። “በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” በማለት ለኢየሱስ ሰገዱለት።

**የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 14፡22-23፤ ማርቆስ 6፡45-52፤ ዮሐንስ 6፡16-21።**

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).