32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ

32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ — illustration 1

አንድ ቀን ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በጀልባ ሐይቁን አቋርጠው የጌርጌሴኖን ሰዎች ወደሚኖሩበት አካባቢ ሄዱ።

32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ — illustration 2

ወደ ሐይቁ ማዶ በደረሱ ጊዜ ርኵስ መንፈስ የያዘው ሰው ሮጦ ወደ ኢየሱስ መጣ።

32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ — illustration 3

ይህ ሰው ማንም ሊቈጣጠረው የማይችል እጅግ ብርቱ ነበረ። ሰዎች እጆቹንና እግሮቹን እንኳ በሰንሰለት አስረውት ነበር፣ ነገር ግን ሰንሰለቱን ይበጣጥስ ነበር።

32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ — illustration 4

ሰውዬው በአካባቢው ባሉ መቃብሮች መካከል ይኖር ነበር። ይህ ሰው ቀኑንና ሌሊቱን ሁሉ ይጮኽ ነበር። ልብስ አይለብስም ነበር፣ ሰውነቱንም በተደጋጋሚ በድንጋይ ይቧጭር ነበር።

32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ — illustration 5

ሰውዬው ወደ ኢየሱስ በመጣ ጊዜ፣ በፊቱ በጉልበቱ ወድቆ ሰገደለት። ኢየሱስ ርኵስ መንፈሱን፣ “ከዚህ ሰው ውጣ!” አለው።

32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ — illustration 6

ርኵስ መንፈሱ ያለበት ሰው ከፍ ባለ ድምፅ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፣ ከእኔ ምን ትፈልጋለህ? እባክህን አታሠቃየኝ!" ብሎ ከፍ ባለ ድምፅ ጮኸ። ከዚያም ኢየሱስ ርኵስ መንፈሱን፣ “ስምህ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም፣ “ብዙዎች ነንና ስሜ ሌጌዎን ነው” አለና መለሰ። (“ሌጌዎን” በሮማ ጦር ሠራዊት ብዙ ሺህ ወታደሮችን የያዘ ክፍል ነበር።)

32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ — illustration 7

ርኵሳን መናፍስቱ፣ “እባክህን ከዚህ አካባቢ አታርቀን!” ብለው ለመኑት። በአቅራቢያው ባለ ኮረብታ ላይ የእሪያ መንጋ ተሰማርቶ ነበር። ስለዚህ ርኵሳን መናፍስቱ ኢየሱስን፣ “እባክህን በዚህ ፈንታ ወደ እሪያዎቹ ስደደን!” ብለው ለመኑት። ኢየሱስ፣ “ሂዱ!” አላቸው።

32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ — illustration 8

ርኵሳን መናፍስቱ ከሰውዬው ወጡና ወደ እሪያዎቹ ገቡ። እሪያዎቹ ከአፋፉ ቊልቊል ሮጡና በሐይቁ ሰጠሙ። በመንጋው 2,000 ያህል እሪያዎች ነበሩ።

32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ — illustration 9

እሪያዎቹን ይጠብቁ የነበሩት ሰዎች የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ ወደ ከተማ ሮጡና ኢየሱስ ያደረገውን ነገር ላገኙት ሰው ሁሉ ተናገሩ። የከተማው ሰዎች መጡና ርኵሳን መናፍስት የነበሩበትን ሰው ዐዩ። ልብሱን ለብሶ እንደ ጤናማ ሰው ሆኖ በጸጥታ ተቀምጦ ነበር።

32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ — illustration 10

ሰዎቹ በጣም ፈርተው ነበርና ኢየሱስን እንዲሄድ ጠየቁት። ስለዚህ ኢየሱስ ጀልባ ውስጥ ገባና ለመሄድ ተዘጋጀ። ርኵን መናፍስት የነበሩበት ሰው ከኢየሱስ ጋር ለመሄድ ልመና አቀረበ።

32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ — illustration 11

ነገር ግን ኢየሱስ፣ “አይደለም፣ ወደ ቤትህ ሄደህ እግዚአብሔር ስላደረገልህ ነገር ሁሉና እንዴት እንደ ማረህ ለወዳጆችህና ለቤተ ሰብህ እንድትነግር እፈልጋለሁ” አለው።

32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ — illustration 12

ስለዚህ ሰውዬው ሄደና ኢየሱስ ስላደረገለት ነገር ለሁሉም ሰው ተናገረ። ታሪኩን የሰማ ሰው ሁሉ በአድናቆትና በአግራሞት ተሞላ።

32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ — illustration 13

ኢየሱስ ወደ ሐይቁ ማዶ ተመለሰ። እዚያ በደረሰ ጊዜ ብዙ ሕዝብ በዙሪያው ተሰበሰቡና አጨናነቁት። በሕዝቡ መካከል ለዐሥራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈሳት የነበረች ሴት ነበረች። እንዲፈውሱአት ገንዘብዋን ሁሉ ለሐኪሞች ከፍላ ነበር፣ ነገር ግን ባሰባት።

32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ — illustration 14

ኢየሱስ ብዙ በሽተኞችን እንደ ፈወሰ ሰምታ ነበርና፣ “የኢየሱስን ልብስ ብቻ ብዳስስ ያኔ እኔም እንደምፈወስ እርግጠኛ ነኝ!” ብላ ዐሰበች። ስለዚህ ከኢየሱስ ኋላ መጣችና ልብሱን ዳሰሰች። ልብሱን እንደ ዳሰሰች ወዲያውኑ ደምዋ ቆመ!

32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ — illustration 15

ወዲያውኑ፣ ኢየሱስ ኃይል ከእርሱ እንደ ወጣ ዐወቀ። ስለዚህ ወደ ኋላ ዞረና፣ “ማን ነው የዳሰሰኝ?” ብሎ ጠየቀ። ደቀ መዛሙርቱ፣ “በዙሪያህ የተሰበሰቡና የሚያጋፉህ ብዙ ሰዎች አሉ። ‘ስለ ምን ማን ዳሰሰኝ’ ብለህ ትጠይቃለህ?” ብለው መለሱለት።

32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ — illustration 16

ሴቲቱ እየተንቀጠቀጠችና በጣም እየፈራች በኢየሱስ ፊት ተደፋች። ከዚያም ያደረገችውን፣ እንዲሁም የተፈወሰች መሆንዋን ነገረችው። ኢየሱስ፣ “እምነትሽ አድኖሻል። በሰላም ሂጂ” አላት።

**የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 8፡28-34፤ 9፡20-22፤ ማርቆስ 5፡1-20፤ 5፡24-34፤ ሉቃስ 8፡26-39፤ 8፡42-48።**

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).