39. ኢየሱስ ለፍርድ ቀረበ

39. ኢየሱስ ለፍርድ ቀረበ — illustration 1

አሁን ጊዜው እኩለ ሌሊት ነው። ሊቀ ካህናቱ ይጠይቀው ዘንድ ወታደሮቹ ኢየሱስን ወደ ሊቀ ካህናቱ ቤት ወሰዱት። ጴጥሮስ ራቅ ብሎ ከኋላ ተከተላቸው። ኢየሱስን ወደ ቤቱ ባስገቡት ጊዜ፣ ጴጥሮስ በውጪ ሆኖ እሳት ይሞቅ ነበር።

39. ኢየሱስ ለፍርድ ቀረበ — illustration 2

በቤቱ ውስጥ የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን ለፍርድ አቀረቡት። ስለ እርሱ የዋሹ ብዙ የሐሰት ምስክሮችን አመጡ። ይሁን እንጂ፣ ቃላቸው እርስ በርሱ አልተስማማም፣ ስለዚህ የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስ በማንኛውም ነገር በደለኛ መሆኑን ማረጋገጥ አልቻሉም።

39. ኢየሱስ ለፍርድ ቀረበ — illustration 3

በመጨረሻ፣ ሊቀ ካህናቱ ኢየሱስን በቀጥታ ተመለከተውና፣ ንገረን፣ አንተ መሲሑ፣ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህን?" አለው።

39. ኢየሱስ ለፍርድ ቀረበ — illustration 4

ኢየሱስ፣ “እኔ ነኝ፣ እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር ተቀምጬና ከሰማይ ስመጣ ታያለህ” አለው። ሊቀ ካህናቱ በቊጣ ልብሱን ቀደደና ወደ ሌሎቹ የሃይማኖት መሪዎች፣ “ተጨማሪ ምስክሮች አያስፈልጉም! የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ሲል ሰምታችሁታል። ፍርዳችሁ ምንድን ነው?” ብሎ ጮኸ።

39. ኢየሱስ ለፍርድ ቀረበ — illustration 5

ሁሉም የአይሁድ መሪዎች፣ “መሞት ይገባዋል!” ብለው ለሊቀ ካህናቱ መለሱለት። ከዚያም ኢየሱስን ፊቱን ሸፈኑት፣ ተፉበት፣ መቱት፣ ዘበቱበትም።

39. ኢየሱስ ለፍርድ ቀረበ — illustration 6

ጴጥሮስ ከቤቱ ውጪ በመጠባበቅ ላይ እያለ የቤት ሠራተኛ የሆነች ልጅ ዐየችውና፣ “አንተም ደግሞ ከኢየሱስ ጋር ነበርክ!” አለችው። ጴጥሮስ እርስዋ የተናገረችውን ካደ። ከዚያ በኋላ ሌላዋ የቤት ሠራተኛ ያንኑ ተናገረች፣ ጴጥሮስም እንደገና ካደ። በመጨረሻ ሕዝቡ “ሁለታችሁም ከገሊላ ስለሆናችሁ አንተ ከኢየሱስ ጋር መሆንህን እናውቃለን” አሉ።

39. ኢየሱስ ለፍርድ ቀረበ — illustration 7

ከዚያም ጴጥሮስ፣ “ይህንን ሰው የማውቀው ከሆነ የእግዚአብሔር መርገም በእኔ ላይ ይሁን! ብሎ ማለ። ወዲያውኑ ዶሮ ጮኸ፣ ኢየሱስም ዘወር አለና ጴጥሮስን ተመለከተው።

39. ኢየሱስ ለፍርድ ቀረበ — illustration 8

ጴጥሮስ ሄደና በምሬት አለቀሰ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ፣ የአይሁድ መሪዎች እንዲሞት በኢየሱስ ላይ እንደ ፈረዱበት ዐየ። ይሁዳ በሐዘን ተሞልቶ ሄደና ራሱን ገደለ።

39. ኢየሱስ ለፍርድ ቀረበ — illustration 9

በነጋታው ማለዳ ላይ የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን ወደ ሮማው ገዥ ወደ ጲላጦስ አመጡት። ጲላጦስ ኢየሱስን ጥፋተኛ ነህ ብሎ ይፈርድበትና በሞት እንዲቀጣ ያደርጋል ብለው ተስፋ አደረጉ። ጲላጦስ ኢየሱስን፣ “የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ብሎ ጠየቀው።

39. ኢየሱስ ለፍርድ ቀረበ — illustration 10

ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፣ “አንተ አልህ፣ ነገር ግን መንግሥቴ ምድራዊ መንግሥት አይደለችም። እንደዚያ ብትሆን ኖሮ፣ አገልጋዮቼ ይዋጉልኝ ነበር። ስለ እግዚአብሔር እውነቱን ለመናገር ወደ ምድር መጥቼአለሁ። እውነትን የሚወድ ሁሉ እኔን ይሰማኛል።” ጲላጦስ፣ “እውነት ምንድን ነው?” አለ።

39. ኢየሱስ ለፍርድ ቀረበ — illustration 11

ጲላጦስ ከኢየሱስ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወደ ሕዝቡ ወጣና፣ “በዚህ ሰው ላይ ምንም በደል አላገኘሁበትም” አለ። የአይሁድ መሪዎችና ሕዝቡ ግን፣ “ስቀለው!” ብለው ጮኹ። ጲላጦስ፣ “በደለኛ አይደለም” ብሎ መለሰላቸው። እነርሱ ግን የበለጠ ጮኹ። ከዚያም ጲላጦስ ለሦስተኛ ጊዜ፣ “በደል የለበትም!” አለ።

39. ኢየሱስ ለፍርድ ቀረበ — illustration 12

ጲላጦስ ሕዝቡ መረበሽ ይጀምራሉ ብሎ ፈራ፣ ስለዚህ ኢየሱስን እንዲሰቅሉት ወታደሮቹን አዘዘ። የሮማ ወታደሮች ኢየሱስን ገረፉትና ቀይ ልብስ አለበሱት፣ እንዲሁም የሾኽ አክሊል በራሱ ላይ አደረጉ። ከዚያም፣ “እነሆ፣ የአይሁድ ንጉሥ!” በማለት ዘበቱበት።

**የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 26፡57-27፡26፤ ማርቆስ 14፡53-15፡15፤ ሉቃስ 22፡54-23፡25፤ ዮሐንስ 18፡12-19፡16።**

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).