4. የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከአብርሃም ጋር

4. የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከአብርሃም ጋር — illustration 1

ከጥፋት ውሃው ከብዙ ዓመታትበኋላ ሕዝቦች በዓለም ላይ እንደገና በዙ።ሁሉም አንድ አይነትቋንቋ ይናገሩ ነበር። እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው ምድርን ከመሙላትይልቅ በአንድነት ተሰብስበውከተማ ሠሩ።

4. የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከአብርሃም ጋር — illustration 2

እነርሱም በጣም ትምክህተኞችና እግዚአብሔር ለተናገራቸው ነገር ያልተጠነቀቁ ነበሩ። እንዲያውም ወደ ሰማይ ሊደርሱ ረጅም ሕንጻ መገንባት ጀመሩ። እግዚአብሔርም እነዚህ ሰዎች ክፉ መሥራታቸውንና በዚህም መቀጠላቸውን አየ። ከዚህም የከፋ ኃጢአት ማድረግ ይችሉም ነበር።

4. የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከአብርሃም ጋር — illustration 3

ስለዚህም እግዚአብሔር ቋንቋቸውን ወደ ብዙ የተለያዩ ቋንቋዎች ለወጠና ሕዝቡን በዓለም ሁሉ በተናቸው። ሊሠሩት የጀመሩት ከተማ ስም ባቢሎን ይባላል። የስሙም ትርጓሜ የተደባለቀ ወይም ግራ የተጋባ ማለት ነው።

4. የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከአብርሃም ጋር — illustration 4

ከመቶ ዓመታት በኋላ እግዚአብሔር አብራም የተባለውን ሰው ተናገረው። እግዚአብሔርም እንዲህ አለው አገርህንና ቤተ ሰብህን ትተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ። በዚያም እባርክሃለሁ፣ ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ ስምህንም ታላቅ አደርገዋለሁ፣ የሚባርኩህን እባርካለሁ፣ የሚረግሙህንም እረግማለሁ ባንተ ምክንያትም የምድር ሰዎች ሁሉ ይባረካሉ።

4. የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከአብርሃም ጋር — illustration 5

አብራምም እግዚአብሔርን ታዘዘ ሚስቱን ሦራንና አገልጋዮቹን ሁሉና ንብረቱንም ሁሉ ይዞ እግዚአብሔር ወዳሳየው የከነዓን ምድር ሄደ።

4. የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከአብርሃም ጋር — illustration 6

አብራም ከነዓን በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር “በዙሪያህ ያለውን ሁሉ ተመልከት የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘሮችህ ውርስ አድርጌ እሰጣችኋለሁ” አለው። አብራምም በምድር ተቀመጠ።

4. የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከአብርሃም ጋር — illustration 7

ከዕለታት አንድ ቀን አብራም መልከ ጼዴቅ የተባለውን ታላቁን የእግዚአብሔር ሊቀ ካህናት ተገናኘው። መልከ ጻዴቅም አብራምን ባረከው እንዲህም አለው “የሰማይና የምድር ጌታ ታላቁ እግዚአብሔር አብራምን ይባርክ” አብራምም ለመልከ ጼዴቅ ካለው ሁሉ አሥራት ሰጠው።

4. የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከአብርሃም ጋር — illustration 8

ብዙ ዓመታት ቢያልፉም አብራምና ሦራ አሁንም ያለ ልጅ ይኖሩ ነበር። እግዚአብሔር ለአብራም እንደ ገና ተስፋ ሰጠው ልጅ እንደሚኖረውና ዘሮቹ እንደ ሰማይ ክዋክብት እንደሚበዙ ተናገረው። አብራምም በእግዚአብሔር ተስፋ አመነ። አብራምም በእግዚአብሔር ተስፋ በማመኑ ምክንያት ጻድቅ ሆኖ ተቈጠረ።

4. የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከአብርሃም ጋር — illustration 9

እግዚአብሔርምከአብራም ጋር ቃልኪዳን አደረገ። ቃልኪዳን በሁለት ወገኖች መካከል የሚደረግ ስምምነት ነው። እግዚአብሔርም አብራምን“ከገዛ አብራክህ ልጅእሰጥሃለሁ” አለው።“ለዘሮችህም የከነዓንን ምድር እሰጣለሁ።” አብራምግን በዚያን ጊዜ ያለ ልጅ ነበር።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 11-15

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).