3. የጥፋት ውሃ

3. የጥፋት ውሃ — illustration 1

ከረጅም ጊዜ በኋላ ብዙ ሕዝቦች በዓለም ይኖሩ ነበር። እነርሱም በጣም ክፉዎችና ኃይለኞች ሆኑ። ክፋትም በጣም እየበዛ በመምጣቱ እግዚአብሔር ዓለምን ሁሉ በሚያጥለቀልቅ የጥፋት ውሃ አጠፋለሁ ሲል ወሰነ።

3. የጥፋት ውሃ — illustration 2

ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን አገኘ። ኖኅ በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች ሁሉይልቅ ጻድቅና ከበደል የራቀ ሰው ነበር።እግዚአብሔርም ሊልክ ስላቀደው የጥፋት ውሃለኖኅ ነገረው። ኖኅ ግዙፍ መርከብ እንዲሠራ እግዚአብሔርነገረው።

3. የጥፋት ውሃ — illustration 3

እግዚአብሔርም ለኖኅ መርከብ እንዲሠራ ነገረው። የመርከቢቱም ርዝመት 140 ሜትር ወርዷ 23 ሜትር ከፍታዋ 13.5 ሜትር ይሁን አለ። ኖኅ የሚሠራት መርከብ ከእንጨት የተሠራች ሆና ባለ ሦስት ፎቅ፤ ብዙ ክፍሎች ጣራና መስኮት ያሉአት ነበረች፤ መርከቢቱም ኖኅንና ቤተ ሰቡን፣ ሁሉንም ዓይነት የምድር ላይ እንስሳት ከጥፋት ውሃ እንድትጠብቅ ነገረው።

3. የጥፋት ውሃ — illustration 4

ኖኅም እግዚአብሔርን በመታዘዘ እግዚአብሔር እንደ ነገራቸውም ኖኅና ሦስቱ ልጆቹ መርከቢቱን ሠሩ። መርከቧ በጣም ትልቅ ነበረችና ሲሠራ ብዙ ዓመታት ፈጀ። ኖኅ ስለሚመጣው የጥፋት ውሃ ለሕዝቡ እያስጠነቀቀ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ ይነግራቸው ነበር ይሁን እንጂ አላመኑትም።

3. የጥፋት ውሃ — illustration 5

እግዚአብሔር ኖኅንና ቤተ ሰቡን በቂ ምግብ ለራሳቸውና ለእንስሳቱ እንዲያከማቹ አዘዘ ሁሉም ነገር ዝግጁ በሆነ ጊዜ ወደ መርከቢቱ ለመግባት ለኖኅ፣ ለሚስቱ፣ ለሦስቱ ወንዶች ልጆቹና ለሚስቶቻቸው ጊዜው መድረሱን ነገረው። ስምንት ሰዎችም ወደ መርከቢቱ ገቡ።

3. የጥፋት ውሃ — illustration 6

እግዚአብሔር ከጥፋት ውሃው እንዲጠበቁ የሁሉንም ተባእትና እንስት እንስሳት ወፎችን ጨምሮ ወደ ኖኅ ላከ። ለመሥዋዕት የሚያገለግሉ ሰባት ተባእትና ሰባት እንስት ከሁሉም ዓይነት እንስሳ ወደ ኖኅ መርከብ ላካቸው። ሁሉም ወደ መርከቡ እንደ ገቡ እግዚአብሔር ራሱ የመርከቡን በር ዘጋ።

3. የጥፋት ውሃ — illustration 7

ከዚያም ዝናቡ መዝነብ ጀመረ፣ ዘነበ፣ ዘነበ፣ ዘነበ ያለማቋረጥ ለ40 ቀንና ሌሊት ዘነበ፣ ከምድርም ምንጭ ይፈልቅ ነበር። በመላው ዓለም ያለው ሁሉም ነገር በውሃ ተሸፈነ፤ ረጃጅም ተራሮች እንኳ ሳይቀሩ በውሃ ተሸፈኑ።

3. የጥፋት ውሃ — illustration 8

በመርከቡ ከነበሩት ሰዎችና እንስሳት በቀር በምድር ይኖር የነበረ ነገር ሁሉ ሞተ፤ መርከቢቱም በውሃው ላይ ተንሳፍፋ በውስጧ የሚገኙትን ነፍሳት ሁሉ ከሞት አዳነች (አተረፈች)።

3. የጥፋት ውሃ — illustration 9

ዝናቡ መዝነቡን ካቆመ በኋላ መርከቢቱ ለአምስት ወራት ያህል በውሃው ላይ ተነሳፈፈች። በዚህም ጊዜ ውሃው መቀነስ ጀመረ። ከዕለታት አንድ ቀን መርከቢቱ በተራራው አናት ላይ አረፈች፤ ይሁን እንጂ ዓለም አሁንም በውሃ ተሸፍና ነበር። ከሦስት ወራት በኋላ የተራራ ጫፎች መታየት ጀመሩ።

3. የጥፋት ውሃ — illustration 10

ከአርባ ቀናት በኋላ ኖኅ ውሃው ከምድር ላይ ደርቆ እንደ ሆነ እንዲያይ ቁራ የተባለን ወፍ/አሞራ ላከ። ቁራው እዚህም እዚያም እየበረረ ደረቅ መሬት ቢፈልግም ሊያገኝ አልቻለም።

3. የጥፋት ውሃ — illustration 11

በኋላም ኖኅ ርግብ የተባለች ወፍ ላከ። ይሁን እንጂ የምታርፍበት መሬት ማግኘት ስላልቻለች ወደ ኖኅ ተመልሳ መጣች። ከሳምንት በኋላ ኖኅ እንደ ገና ርግቧን ላካት። እርሷም የወይራ ቅጠል በአፏ ይዛ ተመለሰች ውሃው ይቀንስ ስለ ነበር ተክሎችም ደግሞ መብቀል ጀመሩ።

3. የጥፋት ውሃ — illustration 12

ኖኅ ሌላ አንድ ሳምንት ጠብቆ ርግቢቷን ለሦስተኛ ጊዜ ሰደዳት፤ በዚህ ጊዜ የምታርፍበት ስፍራ ስላገኘች ተመልሳ አልመጣችም። ውሃው ይደርቅ ነበር።

3. የጥፋት ውሃ — illustration 13

ከሁለት ወራት በኋላ እግዚአብሔር ኖኅን አንተ ቤተ ሰብህና እንስሳቱ በሙሉ ከመርከቧ ውጡ አለው። ቤተ ሰቡ ከመርከቢቱ ወጡ። ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆችን ወለዱ ምድርንም ሞሉአት።

3. የጥፋት ውሃ — illustration 14

ኖኅም ከመርከቢቱ ከወጣ በኋላ መሠዊያ ሠራና ከእያንዳንዱ እንስሳ ለመሥዋዕት ሊቀርቡ የሚችሉትን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረበ። እግዚአብሔርም በመሥዋዕቱ ተደሰተ ኖኅንና ቤተ ሰቡን ባረካቸው።

3. የጥፋት ውሃ — illustration 15

እግዚአብሔርም አለ። “ሰዎች ስለሚያደርጉት ክፉ ነገር ዳግም ምድርን ፈጽሞ ላልረግማት ቃል እገባለሁ። ምንም እንኳ ሰዎች ከልጅነታቸው ጀምሮ ኃጢአተኞች ቢሆኑም ዓለምን ዳግመኛ በጥፋት ውሃ አላጠፋም” አለ።

3. የጥፋት ውሃ — illustration 16

እግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ምልክት ይሆን ዘንድ የመጀመሪያውን ቀስተ ደመና ሠራ። ሁልጊዜ ቀስተ ደመናው በሰማይ ላይ ይታያል። እግዚአብሔር በዚህ ቀስተ ደመና አማካይነት ለሕዝቡ የገባውን ኪዳን ያሳታውሳል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 6-8

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).