41. እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሙታን አስነሣው

41. እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሙታን አስነሣው — illustration 1

ወታደሮቹ ኢየሱስን ከሰቀሉት በኋላ፣ የማያምኑት የአይሁድ መሪዎች ጲላጦስን፣ “ያ ውሸታም፣ ኢየሱስ፣ ከሦስት ቀን በኋላ ከሙታን እነሣለሁ ብሎአል። ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን እንዳይሰርቁትና ከሙታን ተነሣ እንዳይሉ ለማረጋገጥ አንድ ሰው መቃብሩን መጠበቅ አለበት” አሉት።

41. እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሙታን አስነሣው — illustration 2

ጲላጦስ፣ “አንዳንድ ወታደሮችን ውሰዱና መቃብሩን በተቻለ መጠን እንዲጠበቅ አድርጉ” አለ። ስለዚህ በመቃብሩ መግቢያ ባለው ድንጋይ ላይ ማኅተም አደረጉና ሥጋውን ማንም እንዳይሰርቀው ለማረጋገጥ በዚያ ወታደሮችን አቆሙ።

41. እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሙታን አስነሣው — illustration 3

ኢየሱስ ከተሰቀለ በኋላ የነበረ ቀን ሰንበት ነበረ። አይሁድ በዚያ ቀን ወደ መቃብር እንዲሄዱ አይፈቀድላቸውም ነበር። ስለዚህ ከሰንበት ቀን በኋላ በማለዳ ብዙ ሴቶች ሥጋው ላይ ተጨማሪ ሽቱ ለማርከፍከፍ ወደ ኢየሱስ መቃብር ሊሄዱ ተዘጋጁ።

41. እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሙታን አስነሣው — illustration 4

በድንገትም ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ። እንደ መብረቅ የሚያበራ መልአክ ከሰማይ ታየ። የመቃብሩን መግቢያ ከድኖ የነበረውን ድንጋይ አንከባለለና ተቀመጠበት። መቃብሩን ይጠብቁ የነበሩት ወታደሮች ፈሩና እንደ ሞቱ ሰዎች ሆነው መሬት ላይ ወደቁ።

41. እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሙታን አስነሣው — illustration 5

ሴቶቹ ወደ መቃብሩ በደረሱ ጊዜ መልአኩ፣ “አትፍሩ ኢየሱስ እዚህ የለም። ልክ እነሣለሁ ብሎ እንደ ተናገረው ከሙታን ተነሥቶአል! መቃብሩን ተመልከቱና እዩ” ብሎ ነገራቸው። ሴቶቹ ወደ መቃብሩ ውስጥ ተመለከቱና የኢየሱስን ሥጋ ያኖሩበትን ስፍራ ዐዩ። ሥጋው በዚያ አልነበረም!

41. እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሙታን አስነሣው — illustration 6

ከዚያም መልአኩ ለሴቶቹ፣ “ሂዱና ‘ኢየሱስ ከሙታን ተነሥቶአል ቀድሞአችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው’” ብሎ ነገራቸው።

41. እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሙታን አስነሣው — illustration 7

ሴቶቹ በፍርሃትና በታላቅ ደስታ ተሞልተው ነበር። የምሥራቹን ለደቀ መዛሙርቱ ለመንገር እየሮጡ ሄዱ።

41. እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሙታን አስነሣው — illustration 8

ሴቶቹ የምሥራቹን ለደቀ መዛሙርቱ ለመንገር በመሄድ ላይ እያሉ፣ ኢየሱስ ታያቸው፣ እነርሱም ሰገዱለት። ኢየሱስ፣ “አትፍሩ። ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለደቀ መዛሙርቴ ንገሩአቸው። በዚያ ያዩኛል” አላቸው።

**የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 27፡62-28፡15፤ ማርቆስ 16፡1-11፤ ሉቃስ 24፡1-12፤ ዮሐንስ 20፡1-18።**

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).