42. ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ

42. ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ — illustration 1

ኢየሱስ ከሙታን በተነሣበት ቀን ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱ በአቅራቢያው ወዳለች ከተማ እየሄዱ ነበር። ሲጓዙም፣ በኢየሱስ ላይ ስለ ደረሰው ነገር ተነጋገሩ። እርሱ መሲሕ እንደ ሆነ ተስፋ አድርገው ነበር፣ ነገር ግን ያኔ እርሱ ተገደለ። አሁን ሴቶቹ እንደ ገና ሕያው ሆኖአል አሉ። ሁለቱ ደቀ መዛሙርት የሚያምኑትን ነገር ዐላወቁም።

42. ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ — illustration 2

ኢየሱስ ወደ እነርሱ ቀረበና አብሮአቸው ይጓዝ ጀመር፣ እነርሱ ግን ዐላወቁትም። ስለ ምን ይነጋገሩ እንደ ነበረ ጠየቃቸው፣ እነርሱም ባለፉት ጥቂት ቀናት ኢየሱስን በሚመለከት ስለ ሆኑት አስደናቂ ነገሮች ሁሉ ነገሩት። በኢየሩሳሌም የሆነውን ነገር ከማያውቅ እንግዳ ጋር ይነጋገሩ እንደ ነበር ዐሰቡ።

42. ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ — illustration 3

ከዚያም ኢየሱስ፣ ስለ መሲሑ የእግዚአብሔር ቃል የተናገረውን አብራራላቸው። መሲሑ መከራ እንደሚቀበልና እንደሚገደል፣ ነገር ግን በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ነቢያት የተናገሩትን አስታወሳቸው። ሁለቱ ሰዎች ሊያድሩባት ወዳሰቡአት ከተማ ሲደርሱ፣ ጊዜው ሊመሽ ምንም ያህል አልቀረውም ነበር።

42. ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ — illustration 4

ሁለቱ ሰዎች ከእነርሱ ጋር እንዲያድር ጋበዙት፣ እርሱም ግብዣቸውን ተቀበለ። እራት ለመብላት በተዘጋጁ ጊዜ ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ እግዚአብሔርን አመሰገነ፣ ከዚያም ቈረሰው። በድንገትም ኢየሱስ መሆኑን ዐወቁ። ነገር ግን በዚያን ጊዜ እርሱ ከዓይናቸው ተሰወረ።

42. ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ — illustration 5

ሁለቱ ሰዎች፣ “ኢየሱስ ነው! የእግዚአብሔርን ቃል ሲያብራራልን ልባችን ሲቃጠልብን የነበረው ስለዚህ ነው!” ተባባሉ። ወዲያውኑ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። በደረሱ ጊዜም ለደቀ መዛሙርቱ፣ “ኢየሱስ ሕያው ነው! ዐይተነዋል!” ብለው ነገሩአቸው።

42. ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ — illustration 6

ደቀ መዛሙርቱ እየተነጋገሩ እያሉ፣ ኢየሱስ በድንገት በነበሩበት ክፍል በመካከላቸው ታየና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። ደቀ መዛሙርቱ መንፈስ መሰላቸው፣ ኢየሱስ ግን፣ “ለምን ትፈራላችሁ ትጠራጠራላችሁም? እጆቼንና እግሮቼን እዩ። መናፍስት እንደ እኔ አካል የላቸውም” አላቸው። መንፈስ አለመሆኑን ለማረጋገጥ የሚበላ ነገር እንዲሰጡት ጠየቃቸው። እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቊራጭ ሰጡት፣ በላም።

42. ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ — illustration 7

ኢየሱስም፣ “በእግዚአብሔር ቃል ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ መፈጸም አለበት ብዬ ነግሬአችኋለሁ” አለ። በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲረዱ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው። “መሲሑ መከራ እንደሚቀበል፣ እንደሚሞት፣ በሦስተኛው ቀን ከሙታን እንደሚነሣ ከረጅም ዘመን በፊት ተጽፎአል” አላቸው።

42. ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ — illustration 8

“ደግሞም በመጻሕፍት የኃጢአታቸውን ይቅርታ ለማግኘት ሰዎች ሁሉ ንስሐ ይገቡ ዘንድ ደቀ መዛሙርቴ እንደሚያውጁ ተጽፎአል። እነርሱ ከኢየሩሳሌም ጀምሮ ይህን ያደርጋሉ፣ ከዚያም በሁሉም ስፍራ ወዳሉ የሕዝብ ወገኖች ሁሉ ይሄዳሉ። እናንተ የእነዚህ ነገሮች ምስክሮች ናችሁ።

42. ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ — illustration 9

በቀጣዮቹ አርባ ቀናት ኢየሱስ ብዙ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ታያቸው። አንዴ ከ500 ለሚበልጡ ሰዎች በአንድ ጊዜ ታይቶአል! ሕያው መሆኑን በብዙ መንገድ ለደቀ መዛሙርቱ አረጋገጠላቸው፣ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም አስተማራቸው።

42. ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ — illustration 10

ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፣ “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል። ስለዚህ ሂዱ፣ የሕዝብ ወገኖችን ሁሉ በአብ፣ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፣ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲፈጽሙ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርቴ አድርጓቸው። እኔ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር እንደምሆን አስታውሱ።”

42. ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ — illustration 11

ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ ከአርባ ቀናት በኋላ ደቀ መዛሙርቱን፣ “መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በመጣ ጊዜ አባቴ ኃይልን እስኪሰጣችሁ ድረስ በኢየሩሳሌም ቆዩ” አላቸው። ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ወጣ፣ ደመናም ከዓይናቸው ሰወረችው። ኢየሱስ በፍጥረት ሁሉ ላይ ሊገዛ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ።

**የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 28፡16-20፤ ማርቆስ 16፡12-20፤ ሉቃስ 24፡13-53፤ ዮሐንስ 20፡19-23፤ የሐዋርያት ሥራ 1፡1-11።**

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).