43. ቤተ ክርስቲያን ተጀመረች

43. ቤተ ክርስቲያን ተጀመረች — illustration 1

ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከተመለሰ በኋላ፣ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ እንዳዘዛቸው በኢየሩሳሌም ቆዩ። በዚያ የነበሩት አማኞች ለመጸለይ ያለ ማቋረጥ ተሰበሰቡ።

43. ቤተ ክርስቲያን ተጀመረች — illustration 2

አይሁድ በያመቱ ከፋሲካ በኋላ ባሉት 50 ቀናት ጴንጤቆስጤ ተብሎ የሚጠራ አስፈላጊ ቀን ያከብሩ ነበር። ጴንጤቆስጤ አይሁድ የመከር በዓልን የሚያከብሩበት ቀን ነበር። አይሁድ ጴንጤቆስጤን በአንድነት ለማክበር ከመላው ዓለም ወደ ኢየሩሳሌም ይመጡ ነበር። በዚህ ዓመት፣ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከተመለሰ ከአንድ ሳምንት ገደማ በኋላ የጴንጤቆስጤ ጊዜ መጣ።

43. ቤተ ክርስቲያን ተጀመረች — illustration 3

አማኞቹ ሁሉ በአንድነት ተሰብስበው እያሉ፣ በድንገት የነበሩበት ቤት ድምፅ በመሰለ ብርቱ ነፋስ ተሞላ። ከዚያም በአማኞቹ ሁሉ ራስ ላይ የእሳት ነበልባል የሚመስል ነገር ታየ። ሁላቸውም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉና በሌሎች ቋንቋዎች መናገር ጀመሩ።

43. ቤተ ክርስቲያን ተጀመረች — illustration 4

በኢየሩሳሌም የነበሩት ሰዎች ድምፅን በሰሙ ጊዜ፣ በመሆን ላይ የነበረውን ነገር ለማየት በብዛት መጡ። አማኞቹ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራዎች ሲያውጁ ሰዎቹ በሰሙ ጊዜ እነዚህን ነገሮች በገዛ ራሳቸው ቋንቋ በመስማታቸው ተደነቁ።

43. ቤተ ክርስቲያን ተጀመረች — illustration 5

አንዳንዶቹ ሰዎች ደቀ መዛሙርቱ ሰክረዋል ብለው ወቀሱአቸው። ነገር ግን ጴጥሮስ ቆመና እንዲህ አላቸው፣ “ስሙኝ! እነዚህ ሰዎች አልሰከሩም! እግዚአብሔር በነቢዩ ኢዮኤል ‘በመጨረሻው ቀን መንፈሴን አፈስሳለሁ!’ ያለው ትንቢት በዚህ ይፈጸማል።

43. ቤተ ክርስቲያን ተጀመረች — illustration 6

“የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ እናንተ እንዳያችሁትና አስቀድማችሁ እንደምታውቁት ኢየሱስ በእግዚአብሔር ኃይል ብዙ ታላላቅ ምልክቶችንና ድንቆችን ያደረገ ሰው ነው። ነገር ግን እናንተ ሰቀላችሁት!”

43. ቤተ ክርስቲያን ተጀመረች — illustration 7

“ኢየሱስ ቢሞትም እንኳ እግዚአብሔር ከሙታን አስነሣው። ይህም ‘ቅዱስህንም በመቃብር መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም’ የሚለው ትንቢት ፍጻሜ ነው። እግዚአብሔር ኢየሱስን ሕያው አድርጎ እንዳስነሣው እኛ ምስክሮች ነን።”

43. ቤተ ክርስቲያን ተጀመረች — illustration 8

“ኢየሱስ አሁን በእግዚአብሔር አብ ቀኝ ከፍ ብሎአል። ደግሞም ኢየሱስ ልክ ተስፋ እንደ ሰጠው መንፈስ ቅዱስን ልኮአል። አሁን የምታዩአቸውንና የምትሰሙአቸውን ነገሮች መንፈስ ቅዱስ ነው ያደረጋቸው።

43. ቤተ ክርስቲያን ተጀመረች — illustration 9

“ይህንን ኢየሱስን ሰቀላችሁት። ነገር ግን እግዚአብሔር ኢየሱስን ጌታና መሲሕ እንዳደረገው በእርግጥ እወቁ!”

43. ቤተ ክርስቲያን ተጀመረች — illustration 10

ጴጥሮስን ይሰሙ የነበሩት ሰዎች በተናገራቸው ነገሮች በእጅጉ ተነኩ። ስለዚህ ጴጥሮስንና ደቀ መዛሙርቱን፣ “ወንድሞች ሆይ፣ ምን እናድርግ?” ብለው ጠየቁአቸው።

43. ቤተ ክርስቲያን ተጀመረች — illustration 11

ጴጥሮስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ “እግዚአብሔር ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ እያንዳንዳችሁ ንስሐ ግቡና በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ። ከዚያ በኋላ እርሱ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ደግሞ ይሰጣችኋል።”

43. ቤተ ክርስቲያን ተጀመረች — illustration 12

3000 የሚያህሉ ሰዎች ጴጥሮስ የተናገረውን አምነው የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሆኑ። እነርሱ ተጠምቀው በኢየሩሳሌም ያለችው ቤተ ክርስቲያን አባል ሆኑ።

43. ቤተ ክርስቲያን ተጀመረች — illustration 13

ደቀ መዛሙርቱ ያለ ማቋረጥ የሐዋርያትን ትምህርት ሰሙ፣ አብረው ጊዜ አሳለፉ፣ አብረው በሉ፣ አንዳቸው ለሌላኛው ጸለዩ። አብረው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፣ የነበራቸውንም ነገር ሁሉ እርስ በርስ ተካፈሉ። ሁሉም ሰው ስለ እነርሱ መልካም ያስብ ነበር። በየዕለቱ ብዙ ሰዎች አማኞች ሆኑ።

**የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከሐዋርያት ሥራ 2።**

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).