50. ኢየሱስ ይመለሳል

50. ኢየሱስ ይመለሳል — illustration 1

ለ2,000 ዓመታት ያህል በዓለም ዙሪያ ያሉ ብዙ ሰዎች ስለ መሲሑ ኢየሱስ የሚናገረውን የምሥራች እየሰሙ ቈይተዋል። ቤተ ክርስቲያን እያደገች ኖራለች። ኢየሱስ በዓም ፍጻሜ እንደሚመለስ ተስፋ ሰጥቶአል። እርሱ ገና ባይመለስም እንኳ፣ ተስፋውን ይጠብቃል።

50. ኢየሱስ ይመለሳል — illustration 2

የኢየሱስን መመለስ እየተጠባበቅን እያለን፣ እግዚአብሔር ቅዱስ በሆነና እርሱን በሚያስከብረው መንገድ እንድንኖር ይፈልጋል። ደግሞም ስለ መንግሥቱ ለሌሎች እንድንናገር ይፈልጋል። ኢየሱስ በምድር ላይ ይኖር በነበረበት ጊዜ፣ “ደቀ መዛሙርቴ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት የሚናገረውን የምሥራች በዓለም በሁሉም ስፍራ ላሉ ሰዎች ይሰብካሉ፣ በዚያን ጊዜ መጨረሻው ይመጣል” አለ።

50. ኢየሱስ ይመለሳል — illustration 3

ብዙ የሕዝብ ወገኖች አሁንም ስለ ኢየሱስ አልሰሙም። ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከመመለሱ በፊት፣ የምሥራቹን ከቶ ላልሰሙት ሰዎች እንዲያውጁ ለክርስቲያኖች ነገራቸው። “ሂዱና የሕዝብ ወገኖችን ሁሉ ደቀ መዛሙርት አድርጉአቸው!” “መከሩም ደርሶአል!” አለ።

50. ኢየሱስ ይመለሳል — illustration 4

ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም። ልክ የዚህ ዓለም ባለ ሥልጣናት እኔን እንደ ጠሉኝ፣ በእኔ ምክንያት ያሠቃዩአችሁና ይገድሉአችኋል። ምንም እንኳ በዚህ ዓለም መከራ ብትቀበሉም፣ አይዞአችሁ ምክንያቱም እኔ ይህን ዓለም የሚገዛውን ሰይጣንን አሸንፌዋለሁ። እናንተ በእኔ አምናችሁ እስከ መጨረሻ ብትጸኑ፣ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ያድናችኋል!”

50. ኢየሱስ ይመለሳል — illustration 5

ኢየሱስ የዓለም ፍጻሜ በሚሆንበት ጊዜ፣ በሰዎች ላይ የሚደርሰውን ነገር ለማብራራት ለደቀ መዛሙርቱ አንድ ታሪክ ነገራቸው። አንድ ሰው በእርሻው መልካም ዘርን ዘራ። ተኝቶ እያለ ጠላቱ መጣና በስንዴው ላይ የአረም ዘር ዘራበትና ሄደ።"

50. ኢየሱስ ይመለሳል — illustration 6

“የተዘራው ስንዴ በበቀለ ጊዜ፣ የሰውዬው አገልጋዮች፣ ‘ጌታው፣ በዚያ እርሻ መልካም ዘር ዘርተህ ነበር። ታዲያ በውስጡ ለምንድን ነው አረም ያለበት?’ ብለው ጠየቁት፣ጌታውም፣ ‘የዘራው ጠላት መሆን አለበት’” ብሎ መለሰላቸው።

50. ኢየሱስ ይመለሳል — illustration 7

“አገልጋዮቹ ለጌታቸው፣ ‘አረሙን እንንቀለውን?’ ብለው መለሱለት። ጌታቸው እንዲህ አለ፣ ‘አይደለም። ይህንን ብታደርጉ ስንዴውንም ትነቅሉታላችሁ። እስከ መከር ድረስ ቆዩና አረሙን ሰብስባችሁ አቃጥሉት፣ ስንዴውን ግን በጎተራዬ አከማቹት።’”

50. ኢየሱስ ይመለሳል — illustration 8

ደቀ መዛሙርቱ የታሪኩ ትርጕም አልገባቸውም፣ ስለዚህ እንዲያብራራላቸው ኢየሱስን ጠየቁት። ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “መልካሙን ዘር የዘራው ሰው መሲሑን ይወክላል። እርሻው ዓለምን ይወክላል። መልካሙ ዘር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሰዎች ይወክላል።”

50. ኢየሱስ ይመለሳል — illustration 9

“አረሙ ከክፉው ወገን የሆኑ ሰዎችን ይወክላል። አረሙን የዘራው ጠላት ዲያብሎስን ይወክላል። መከሩ የዓለምን ፍጻሜ ይወክላል፣ አጫጆቹም የእግዚአብሔርን መላእክት ይወክላሉ።

50. ኢየሱስ ይመለሳል — illustration 10

“በዓለም ፍጻሜ፣ መላእክት የዲያብሎስ ወገኖች የሆኑ ሰዎችን ሁሉ በአንድ ላይ ይሰበስቡና ወደሚንቀለቀል እሳት ይጥሉአቸዋል፣ በዚያም ይጮኻሉ አስከፊ በሆነ ሥቃይም ጥርሶቻቸውን ያፋጫሉ። በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ።”

50. ኢየሱስ ይመለሳል — illustration 11

ደግሞም ኢየሱስ ልክ ከዓለም ፍጻሜ በፊት ወደ ምድር እንደሚመለስ ተናገረ። በሄደበት አኳኋን ተመልሶ ይመጣል፣ ይኸውም፣ አካላዊ ሰውነት ይኖረዋል፣ በሰማይ ደመናም ይመጣል። ኢየሱስ በሚመለስበት ጊዜ እያንዳንዱ የሞተ ክርስቲያን ከሙታን ይነሣና በሰማይ ይገናኘዋል።

50. ኢየሱስ ይመለሳል — illustration 12

በዚያን ጊዜ ገና በሕይወት ያሉ ክርስቲያኖች ወደ ሰማይ ይነጠቁና ከሙታን ከተነሡ ሌሎች ክርስቲያኖች ጋር ይቀላቀላሉ። በዚያ ሁላቸውም ከኢየሱስ ጋር ይሆናሉ። ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ከሕዝቡ ጋር ፍጹም በሆነ ሰላምና አንድነት ለዘላለም ይኖራል።

50. ኢየሱስ ይመለሳል — illustration 13

ኢየሱስ በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉ ዘውድ ለመስጠት ተስፋ ሰጥቶአል። እነርሱ ፍጹም በሆነ ሰላም ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም ይኖራሉ ይነግሣሉም።

50. ኢየሱስ ይመለሳል — illustration 14

ነገር ግን እግዚአብሔር በኢየሱስ በማያምኑ ሁሉ ላይ ይፈርዳል። ለዘላለም ወደሚያለቅሱበትና በሥቃይ ጥርሶቻቸውን ወደሚያፏጩበት ወደ ሲኦል ይጥላቸዋል። ከቶ የማይጠፋ እሳት ባለማቋረጥ ያቃጥላቸዋል፣ ትሎችም እነርሱን መብላታቸውን በጭራሽ አያቋርጡም።

50. ኢየሱስ ይመለሳል — illustration 15

ኢየሱስ በሚመለሰበት ጊዜ፣ ሰይጣንና መንግሥቱን ሙሉ በሙሉ ያጠፋቸዋል። ሰይጣንን ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ይልቅ እርሱን ለመከተል ከመረጡት ሁሉ ጋር ለዘላለም ወደሚቃጠሉበት ወደ ሲኦል ይጥለዋል።

50. ኢየሱስ ይመለሳል — illustration 16

አዳምና ሔዋን ለእግዚአብሔር ስላልታዘዙና ኃጢአትን ወደዚህ ዓለም ስላመጡ፣ እግዚአብሔር ዓለምን ረገማት ሊያጠፋትም ወሰነ። ነገር ግን አንድ ቀን እግዚአብሔር ፍጹም የሚሆን ዐዲስ ሰማይና ዐዲስ ምድር ይፈጥራል።

50. ኢየሱስ ይመለሳል — illustration 17

ኢየሱስና ሕዝቡ በዐዲሲቱ ምድር ይኖራሉ፣ ባለው ሁሉ ነገር ላይ ለዘላለም ይነግሣሉ። እርሱ እንባን ሁሉ ያብሳል፣ ከእንግዲህ ሥቃይ፣ ሐዘን፣ ልቅሶ፣ ክፋት፣ ሕመም፣ ወይም ሞት አይኖርም። ኢየሱስ መንግሥቱን በሰላምና በፍትሕ ይገዛል፣ ለዘላለምም ከሕዝቡ ጋር ይሆናል።

**የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 24፡14፤ 28፡18፤ ዮሐንስ 15፡20፤ 16፡33፤ ራእይ 2፡10፤ ማቴዎስ 13፡24-30፤ 36-42፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡13-5፡11፤ ያዕቆብ 1፡12፤ ማቴዎስ 22፡13፤ ራእይ 20፡10፤ 21፡1-22፡21።**

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).