49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 1

አንድ መልአክ ማርያም ለተባለች ድንግል የእግዚአብሔርን ልጅ እንደምትወልድ ነገራት። ስለዚህ እርስዋ ገና ድንግል እያለች ወንድ ልጅ ወለደችና ኢየሱስ ብላ ሰየመችው። ስለዚህ ኢየሱስ አምላክም ሰውም ነው።

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 2

ኢየሱስ አምላክ መሆኑን የሚያረጋግጡ ብዙ ተአምራትን አደረገ። በውሃ ላይ ተራመደ፣ ማዕበልን ጸጥ አደረገ፣ ብዙ በሽተኞችን ፈወሰ፣ አጋንንትን አወጣ፣ ሙታንን አስነሣ፣ እንዲሁም አምስት እንጀራና ሁለት ትንንሽ ዓሣ ከ5,000 ለበለጡ ሰዎች እንዲበቃ አደረገ።

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 3

ደግሞም ኢየሱስ ታላቅ መምህር ነው፣ የእግዚአብሔር ልጅ ስለሆነም በሥልጣን ተናገረ። ራሳችሁን እንደምትወዱ ሌሎችን ሰዎችንም ውደዱ ብሎ አስተማረ።

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 4

ደግሞም እርሱ ሀብታችሁን ጨምሮ ማንኛውንም ነገር እንደምትወዱ እግዚአብሔርን መውደድ አለባችሁ ብሎ አስተማረ።

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 5

ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንግሥት በዓለም ካለ ከማንኛውም ነገር ይልቅ የከበረች ነች አለ። ለማንኛውም ሰው እጅግ በጣም አስፈላጊው ነገር የእግዚአብሔር መንግሥት ወገን መሆን ነው። ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ከኃጢአታችሁ መዳን አለባችሁ።

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 6

ኢየሱስ አንዳንድ ሰዎች ተቀብለውት እንደሚድኑ፣ ሌሎች ግን እንደማይቀበሉት አስተማረ። አንዳንድ ሰዎች እንደ መልካም መሬት ናቸው አለ። የኢየሱስን የምሥራች ተቀብለው ይድናሉ። ሌሎች ሰዎች የእግዚአብሔር ቃል ዘር እንደማይገባበትና ምንም ፍሬ እንደማያፈራ በመንገድ ዳር እንዳለ አለትማ መሬት ናቸው። እነዚያ ሰዎች ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን መልእክት የማይቀበሉና ወደ መንግሥቱ የማይገቡ ናቸው።

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 7

ኢየሱስ፣ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን በጣም እንደሚወድ አስተማረ። ይቅር ሊላቸውና ልጆቹ ሊያደርጋቸው ይፈልጋል።

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 8

ደግሞም ኢየሱስ እግዚአብሔር ኃጢአትን እንደሚጠላ ነግሮናል። አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ፣ ኃጢአቱ ዝርያዎቻቸውን ሁሉ ጐዳ። ከዚህ የተነሣ በዓለም ያለ ሁሉም ሰው ኃጢአት ይሠራል ከእግዚአብሔርም ይለያያል። ስለዚህ ሁሉም ሰው የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 9

ነገር ግን በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 10

በኃጢአታችሁ ምክንያት በደለኞች ናችሁና መሞት ይገባችኋል። እግዚአብሔር በእናንተ ላይ መቈጣት ነበረበት፣ ነገር ግን ቊጣውን በእናንተ ላይ በማፍስስ ፈንታ በኢየሱስ ላይ አፈሰሰው። ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሞተ ጊዜ፣ የእናንተን ቅጣት ተቀበለ።

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 11

ኢየሱስ ከቶ ኃጢአት አላደረገም፣ ነገር ግን የእናንተን ኃጢአትና በዓለም ያለውን የእያንዳንዱን ሰው ኃጢአት ለማስወገድ መቀጣትንና ፍጹም መሥዋዕት ሆኖ መሞትን መረጠ። ኢየሱስ ራሱን ስለ ሠዋ፣ እግዚአብሔር ማንኛውንም ኃጢአት፣ አስከፊ የሆነውን ኃጢአት እንኳ ይቅር ማለት ይችላል።

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 12

መልካም ሥራዎች ሊያድኑአችሁ አይችሉም። ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት እንዲኖራችሁ ልታደርጉ የምትችሉት ምንም ነገር የለም። ኢየሱስ ብቻ ኃጢአታችሁን ሊያጥብ ይችላል። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን፣ በእናንተ ፈንታ በመስቀል ላይ መሞቱን እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው ብቻ ማመን አለባችሁ።

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 13

እግዚአብሔር በኢየሱስ የሚያምነውንና ጌታው አድርጎ የሚቀበለውን ማንኛውንም ሰው ያድናል። ባለ ጠጎች ሆኑ ወይም ድሆች፣ ወንድ ወይም ሴት፣ ሽማግሌ ወይም ወጣት፣ ወይም የትም ብትኖሩ ምንም አይደለም። እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የቅርብ ግንኙነት ሊኖረው ይችል ዘንድ ይወዳችኋል በኢየሱስ እንድታምኑም ይፈልጋል።

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 14

ኢየሱስ እንድታምኑና እንድትጠመቁ ይጋብዛችኋል። ኢየሱስ መሲሕ፣ ብቸኛው የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ታምናላችሁ? ኃጢአተኞች መሆናችሁንና እግዚአብሔር ቢቀጣችሁ የተገባ መሆኑን ታምናላችሁ? ኢየሱስ ኃጢአታችሁን ለማስወገድ በመስቀል ላይ መሞቱን ታምናላችሁ?

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 15

በኢየሱስና እርሱ ለእናንተ በሠራው ሥራ ብታምኑ፣ እናንተ ክርስቲያኖች ናችሁ! እግዚአብሔር ከሰይጣንና ከጨለማ መንግሥት አውጥቶአችሁ በእግዚአብሔር የብርሃን መንግሥት ውስጥ አድርጎአችኋል። እግዚአብሔር ነገሮችን የምታደርጉበትን አሮጌውንና ኃጢአተኛውን መንገዳችሁን አስወግዶ ዐዲስና ጻድቅ የሆነ የአደራረግ መንገድ ሰጥቶአችኋል።

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 16

እናንተ ክርስቲያኖች ናችሁ፣ ኢየሱስ በሠራው ሥራ ምክንያት እግዚአብሔር ኃጢአታችሁን ይቅር ብሎአችኋል። አሁን እግዚአብሔር በጠላቶች ፈንታ የቅርብ ወዳጆች አድርጎ ይቈጥራችኋል።

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 17

የእግዚአብሔር ወዳጆችና የጌታ ኢየሱስ አገልጋዮች ከሆናችሁ፣ ኢየሱስ ለሚያስተምራችሁ ነገር ትታዘዛላችሁ። ክርስቲያኖች ብትሆኑም እንኳ፣ አሁንም ኃጢአት ለመሥራት ትፈተናላችሁ። ነገር ግን እግዚአብሔር የታመነ ነውና ኃጢአታችሁን ብትናዘዙ ይቅር እላችኋለሁ ይላል። ኃጢአትን የምትቃወሙበትን ብርታት ይሰጣችኋል።

49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን — illustration 18

እግዚአብሔር እንድትጸልዩ፣ ቃሉን እንድታጠኑ፣ ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር እንድታመልኩ፣ ያደረገላችሁንም ለሌሎች እንድትነግሩ ይጠይቃችኋል። እነዚህ ነገሮች ሁሉ ከእርሱ ጋር የጠለቀ ግንኙነት እንዲኖራችሁ ይረዱአችኋል።

**የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከሮሜ 3፡21-26፤ 5፡1-11፤ ዮሐንስ 3፡16፤ ማርቆስ 16፡16፤ ቈላስይስ 1፡13-14፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17-21፤ 1ኛ ዮሐንስ 1፡5-10።**

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).