34.ኢየሱስ ሌሎች ታሪኮችን አስተማረ

34.ኢየሱስ ሌሎች ታሪኮችን አስተማረ — illustration 1

ኢየሱስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ሌሎች ብዙ ታሪኮችን አስተማረ። ለምሳሌ፣ እንዲህ አለ፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት ሰው በማሳው የዘራትን የሰናፍጭ ዘር ትመስላለች። እርስዋም ከሁሉ ዘር የምታንስ ነች።”

34.ኢየሱስ ሌሎች ታሪኮችን አስተማረ — illustration 2

“ነገር ግን የሰናፍጭ ዘር ባደገች ጊዜ አዕዋፍ መጥተው እስኪሰፍሩ ድረስ በአትክልት ቦታ ካሉ ተክሎች ሁሉ ትበልጣለች።

34.ኢየሱስ ሌሎች ታሪኮችን አስተማረ — illustration 3

ኢየሱስ ሌላ ታሪክ ተናገረ፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት ሴት ወስዳ ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ከዱቄት ጋር የለወሰችው እርሾ ትመስላለች።

34.ኢየሱስ ሌሎች ታሪኮችን አስተማረ — illustration 4

“ደግሞ የእግዚአብሔር መንግሥት ሰው በእርሻ ውስጥ የሸሸገው መዝገብ ትመስላለች። ሌላ ሰው መዝገቡን አገኘውና እንደ ገና ቀበረው። በጣም በደስታ ተሞልቶ ነበርና ሄዶ ያለውን ነገር ሁሉ ሸጠና በገንዘቡ እርሻውን ገዛው።”

34.ኢየሱስ ሌሎች ታሪኮችን አስተማረ — illustration 5

“ደግሞ የእግዚአብሔር መንግሥት ዋጋዋ እጅግ ውድ የሆነ ዕንቊ ትመስላለች። የዕንቊ ነጋዴ ባገኛት ጊዜ ያለውን ነገር ሁሉ ሸጠና ገዛት።”

34.ኢየሱስ ሌሎች ታሪኮችን አስተማረ — illustration 6

ከዚያ በኋላ ኢየሱስ በራሳቸው መልካም ሥራ ለሚታመኑና ሌሎችን ለሚንቁ አንዳንድ ሰዎች ታሪክ ተናገረ። “ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ። አንዱ ቀረጥ ሰብሳቢ ሲሆን፣ ሌላው የሃይማኖት መሪ ነበር” አለ።

34.ኢየሱስ ሌሎች ታሪኮችን አስተማረ — illustration 7

“የሃይማኖት መሪው እንዲህ ብሎ ጸለየ፣ ‘እግዚአብሔር ሆይ፣ እንደ ሌሎች ሰዎች ሁሉ፣ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፣ እንደዚህ ቀረጥ ሰብሳቢ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ።”

34.ኢየሱስ ሌሎች ታሪኮችን አስተማረ — illustration 8

“ለምሳሌ፣ እኔ በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጾማለሁ፣ ከማገኘውም ገንዘብና ንብረት ሁሉ ከዐሥር አንድ አወጣለሁ።’”

34.ኢየሱስ ሌሎች ታሪኮችን አስተማረ — illustration 9

“ቀረጥ ሰብሳቢው ግን ከሃይማኖት መሪው ራቅ ብሎ ቆመ፣ ወደ ሰማይ እንኳ አልተመለከተም። በዚህ ፈንታ፣ ደረቱን በእጁ እየመታ፣ ‘እግዚአብሔር ሆይ፣ እኔ ኃጢአተኛ ስለ ሆንኩ እባክህን ማረኝ።’”

34.ኢየሱስ ሌሎች ታሪኮችን አስተማረ — illustration 10

ከዚያ በኋላ ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “እውነት እላችኋለሁ፣ እግዚአብሔር የቀረጥ ሰብሳቢውን ጸሎት ሰማና ጻድቅ ነህ አለው። የሃይማኖት መሪውን ጸሎት ግን አልወደደም። እግዚአብሔር ራሱን ከፍ የሚያደርገውን ሁሉ ያዋርዳል፣ ራሱን የሚያዋርደውን ግን ከፍ ያደርጋል።’

**የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 13፡31-33፣ 44-46፤ ማርቆስ 4፡30-32፤ ሉቃስ 13፡18-21፤ 18፡9-14።**

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).