36. የኢየሱስ መልክ ተለወጠ

36. የኢየሱስ መልክ ተለወጠ — illustration 1

አንድ ቀን ኢየሱስ ሦስቱን ደቀ መዛሙርቱን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ያዞ ሊጸልዩ ወደ ረጅም ተራራ ወጡ። ( ዮሐንስ የተባለው ደቀ መዝሙር ኢየሱስን ያጠመቀው ሰው አልነበረም።)

36. የኢየሱስ መልክ ተለወጠ — illustration 2

ኢየሱስ በመጸለይ ላይ እያለ፣ ፊቱ እንደ ፀሐይ አበራ፣ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ፣ በምድር ላይ ያለ ማንኛውም ሰው ሊያነጻው እስከማይችል ድረስ በጣም ነጭ ሆነ።

36. የኢየሱስ መልክ ተለወጠ — illustration 3

በዚያን ጊዜ ሙሴና ነቢዩ ኤልያስ ታዩ። እነዚህ ሰዎች በመቶዎች ከሚቈጠሩ ዓመታት በፊት በምድር ላይ ይኖሩ ነበር። በቅርቡ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው ሞቱ ከኢየሱስ ጋር ተነጋገሩ።

36. የኢየሱስ መልክ ተለወጠ — illustration 4

ሙሴና ኤልያስ ከኢየሱስ ጋር በመነጋገር ላይ እያሉ ጴጥሮስ ኢየሱስን፣ “በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው። አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ እንዲሁም አንድ ለኤልያስ፣ ሦስት መጠለያዎችን እንሥራ” አለው። ጴጥሮስ የሚናገረውን አያውቅም ነበር።

36. የኢየሱስ መልክ ተለወጠ — illustration 5

ጴጥሮስ እየተናገረ እያለ፣ ብሩህ ደመና መጥቶ ከበባቸውና ከደመናው ድምፅ፣ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፣ እርሱን ስሙት” አለ። ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ፈሩና መሬት ላይ ወደቁ።

36. የኢየሱስ መልክ ተለወጠ — illustration 6

ያኔ ኢየሱስ ዳሰሳቸውና፣ “አትፍሩ፣ ተነሡ” አላቸው። ዙሪያቸውን ሲያዩ ከኢየሱስ በቀር ማንም አልነበረም።

36. የኢየሱስ መልክ ተለወጠ — illustration 7

ኢየሱስና ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ከተራራው ወረዱ። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “በዚህ ስለ ሆነው ነገር ገና ለማንም አትናገሩ። እኔ በቶሎ እሞታለሁ፣ ሕያውም እሆናለሁ። ከዚያ በኋላ ለሰዎች መናገር ትችላላችሁ።”

**የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 17፡1-9፤ ማርቆስ 9፡2-8፤ ሉቃስ 9፡28-36።**

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).