37. ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሣ

37. ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሣ — illustration 1

አንድ ቀን ኢየሱስ አልዓዛር በጣም ታሞአል የሚል መልእክት ደረሰው። አልዓዛርና ሁለቱ እኅቶቹ ማርያምና ማርታ የኢየሱስ የቅርብ ወዳጆች ነበሩ። ኢየሱስ ይህንን ወሬ በሰማ ጊዜ፣ “ይህ ሕመም ለእግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም” አለ። ኢየሱስ ወዳጆቹን ይወዳቸው ነበር፣ ነገር ግን ለሁለት ቀናት በነበረበት ስፍራ ቆየ።

37. ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሣ — illustration 2

ሁለቱ ቀናት ካለፉ በኋላ፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ “ወደ ይሁዳ እንሂድ” አላቸው። “ነገር ግን መምህር ሆይ፣”ልክ ከጥቂት ጊዜ በፊት በዚያ ያሉት ሕዝብ ሊገድሉህ ይፈልጉ ነበር!" ብለው ደቀ መዛሙርቱ መለሱለት። ኢየሱስ፣ “ወዳጃችን አልዓዛር አንቀላፍቶአል፣ ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ” አላቸው።

37. ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሣ — illustration 3

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት፣ “ጌታ ሆይ፣ አልዓዛር ተኝቶስ ከሆነ፣ ይድናል” ብለው መለሱለት። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በግልጽ ነገራቸው፣ “አልዓዛር ሞቶአል። እናንተ በእኔ ታምኑ ዘንድ እዚያ ባለመኖሬ ደስ ብሎኛል።”

37. ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሣ — illustration 4

ኢየሱስ አልዓዛር ወደ ተወለደበት ከተማ በደረሰ ጊዜ፣ አልዓዛር ከሞተ አራት ቀን ሆኖት ነበር። ማርታ ኢየሱስን ልትገናኘው ወጣችና እንዲህ አለች፣ “ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትኖር ኖሮ ወንድሜ አይሞትም ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር የምትለምነውን ሁሉ እንደሚሰጥህ አምናለሁ።”

37. ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሣ — illustration 5

ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላት፣ “እኔ ትንሣኤና ሕይወት ነኝ። በእኔ የሚያምን ሁሉ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል። በእኔ የሚያምን ሁሉ ከቶ አይሞትም። ይህን ታምኛለሽን? ማርታ፣”አዎን፣ ጌታ ሆይ! አንተ መሲሑ፣ የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን አምናለሁ" ብላ መለሰችለት።

37. ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሣ — illustration 6

ከዚያም ማርያም መጣች። በኢየሱስ እግር ወደቀችና፣ “ጌታ ሆይ፣ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተም ነበር” አለች። ኢየሱስ፣ “አልዓዛርን ወዴት ነው ያኖራችሁት?” ብሎ ጠየቃቸው። “በመቃብር ነው። ናና እይ” ብለው ነገሩት። ከዚያም ኢየሱስ አለቀሰ።

37. ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሣ — illustration 7

መቃብሩ ዋሻ ነበር፣ ድንጋይም ተገጥሞበት ነበር። ኢየሱስ ወደ መቃብሩ በደረሰ ጊዜ ድንጋዩን አንከባሉት" ብሎ ነገራቸው። ነገር ግን ማርታ፣ “ከሞተ አራት ቀን ሆኖታል። አሁን ይሸታል” አለችው።

37. ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሣ — illustration 8

ኢየሱስ፣ “በእኔ ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርኩሽምን?” አላት። ስለዚህ ድንጋዩን አንከባለሉት።

37. ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሣ — illustration 9

ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ወደ ላይ ተመለከተና፣ “አባት ሆይ፣ ስለምትሰማኝ አመሰግንሃለሁ። አንተ ሁልጊዜ እንደምትሰማኝ ዐውቃለሁ፣ ነገር ግን አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ እዚህ ስለ ቆሙት ስለ እነዚህ ሰዎች ሁሉ ይህን እላለሁ” አለ። ከዚያም ኢየሱስ፣ “አልዓዛር ሆይ፣ ወደ ውጭ ና!” ብሎ ጮኸ።

37. ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሣ — illustration 10

ስለዚህ አልዓዛር ወጣ! በከፈን እንደ ተገነዘ ነበር። ኢየሱስም፣ “ፍቱትና ይሂድ ተዉት!” አላቸው። ከአይሁድ ብዙዎች በዚህ ተአምር ምክንያት በኢየሱስ አመኑ።

37. ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሣ — illustration 11

ነገር ግን የአይሁድ የሃይማኖት መሪዎች ቀኑ፣ ስለዚህ ኢየሱስንና አልዓዛርን እንዴት መግደል እንዳለባቸው ለማቀድ በአንድ ላይ ተሰበሰቡ።

**የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዮሐንስ 11፡1-46።**

Read in the reader

Free to use, adapt, and share under an open license (CC BY-SA 4.0).